በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢካሣ በሥራ ላይ ነው


የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ ጉብኝት በኢትዮጵያ
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ ጉብኝት በኢትዮጵያ

በምህፃር ኢካሣ እየተባለ የሚጠራው ይህ 16ኛው በአፍሪካ የኤድስና የአባለዘር በሽታዎች ዓለምአቀፍ ጉባዔ በሥራ ላይ ነው፡፡

አዲስ አበባ ላይ የጀግና አቀባበል ተደርጎላቸዋል የተባሉት የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ በዓለማችን አንድን የበሽታ ዓይነት ወይም ወረርሽኝ ለመከላከል መጠነ ሰፊ ዘመቻ ሲከፈትና ግዙፍ በጀት ሲመደብ የመጀመሪያ የሆነውን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት የኤድስ ድጋፍ አፋጣኝ መርኃግብር የፈጠሩ ሰው ናቸው፡፡

ምንም እንኳ በዚህ በአሁኑ የሥራ ጉዟቸው ወቅት የጆርጅ ቡሽ እጅ ተይዞ እንዲታሠሩና ለፍርድ እንዲቀርቡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የሚባለው የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን ቢጠይቅም ኤድስን፣ ወባንና ሣንባ ነቀርሣን ለመዋጋት በጋራ በሚካሄዱ መርኃግብሮች ላይ 39 ቢልዮን ዶላር ስላፈሰሰው የፔፕፋር ተግባራቸው እንደኢትዮጵያ ያሉ ኤድስ እጅግ የበረታ ጉዳት ያደረሰባቸው የአፍሪካ ሃገሮች የሚያስታውሷቸው በክብር ነው፡፡

ከዚህ ፀረ-ኤድስ በጀት ኢትዮጵያ በ140 ሆስፒታሎቿ ውስጥ ለምታከናውነው ተግባርና ፀረ-ኤድስ፣ ወባና ሣንባ ነቀርሣ ዘመቻዋ የ1.4 ቢልዮን ዶላር ድጋፍ ተጠቃሚ ሆናለች፡፡

የአሜሪካ ግብር ከፋዮች የለገሡት ገንዘብ የት እንደዋለ እንዲያውቁ ለማድረግ በፔፕፋር የሚደገፉ የኢትዮጵያ ተቋማትን እንደሚጎበኙ ለአሜሪካ ድምፅ የገለፁት ሚስተር ቡሽ “የአሜሪካዊያን ቸርነት ሕይወቶችን ማትረፉን እንዲያውቁ እፈልጋለሁ” ብለዋል፡፡

“የአሜሪካ ሕዝብ ርሕራሄ መገለጫ ከሆኑ ከፍ ያሉ ተግባራት አንዱን አይቻለሁ” ያሉት ቡሽ ይቀጥሉና “ሃገራችን በዓለም ላይ ፊቷን ማዞር የለባትም፡፡ ውጤት የሚያመጡ መርኃግብሮችን እየደገፍን ርሕራሄያችንን ማሣየት አለብን፡፡ ፔፕፋር ውጤታማ ነው፤ ፀረ-ወባ መርኃግብራችን ውጤታማ ነው” ብለዋል ፕሬዚዳንት ቡሽ፡፡

ለተጨማሪ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG