በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የየመን ሁቲ ታጣቂዎች የግሪክ መርከብ ላይ ጥቃት አድርሰናል አሉ


በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በየመን የሁቲ አማፂያን ጥቃት ደርሶበት የነበረው የግሪክ ንብረት የሆነው ላክስ እህል ጭኖ ወደ ኢራን ይጓዝ እንደነበር ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል
በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በየመን የሁቲ አማፂያን ጥቃት ደርሶበት የነበረው የግሪክ ንብረት የሆነው ላክስ እህል ጭኖ ወደ ኢራን ይጓዝ እንደነበር ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል

በኢራን የሚደገፉት የየመን ሁቲ አማጽያን “እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ ራፋህ ከተማ ላይ ለምታደርሰው ጥቃት አጸፋ ለመመለስ የግሪክ ንብረት የሆነ ግዙፍ የዕቃ ማጓጓዣ መርከብ እና ሌሎችም መርከቦች ላይ ጥቃት አድርሰናል” ሲሉ አስታወቁ፡፡

በማርሻል ደሴት ባንዲራ የሚጓዘው የግሪኩ መርከብ ከትላንት በስተያ ማክሰኞ በሦስት ሚሳይሎች መመታቱን እንዳስታወቀ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ኅይል ማዕከላዊ ዕዝ ሴንትኮም እና የመርከብ ጉዞ ደህንነት ኩባኒያዎች አስታውቀዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትሱ ማዕከላዊ ዕዝ እና የብሪታኒያ የባሕር ኅይል የሚያስተዳድረው የዩናይትድ ኪንግደም የማሪታይም ንግድ እንቅስቃሴ ተቋም እንዳስታወቁት መርከቡ ጉዳት ቢደርስበትም ጉዞውን ቀጥሏል፡፡ በአካባቢው ያለው በምዕራብ ሀገሮች የባሕር ኅይሎች ግብረ ኅይል የሚመራው የጋራ የማሪታይም መረጃ ማዕከል እንዳስታወቀው ከመርከቡ ሠራተኞች መካከል አንዱ ጉዳት ደርሶበታል፡፡

የሁቲዎች ወታደራዊ ቃል አቀባይ ያህያ ሳሬ ትላንት ረቡዕ “ኤክስ” ላይ ባወጣው መግለጫ መርከቡ “በቀጥታ ተመትቶ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል” ብሏል፡፡ ታጣቂዎቹ ሌሎች አምስት መርከቦች ላይ ጥቃት አድርሰዋል ሲልም አክሎ ጥቃቱን ያደረስነው “በከበበቻት የጋዛ ሰርጥ ላይ በተከታታይ ጥቃት ስታደርስ የቆየችው ጽዮናዊቱ ጠላት ራፋህ ላይ በሚገኙት ተፈናቃዮች ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት ለመበቀል ነው” ማለቱን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ጠቅሷል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ዕዝ ሁቴዎች በሚመሩት የየመን አካባቢ ሁለት የሚሳይል መወንጨፊያዎችን ማውደሙን እና ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ደግሞ ቀይ ባሕር ላይ ሁለት ሰው አልባ አውሮፕላኖች መትቶ መጣሉን ተናግሯል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG