ኽሊን በመባል የምትጠራው አውሎ ነፋስ የቀላቀለች ዝናብ ትላንት ማምሻውን በፍሎሪዳ ግዛት ደርሳ 3 ሚሊዮን ደንበኞችን ካለ ኤሌክትሪክ ኃይል አስቀርታለች፡፡ አውሎ ነፋሷ ዛሬ ጆርጂያ ግዛት ስትደርስ ኃይሏ እየተዳከመ መምጣቷም ታውቋል።
ኽሊን ትላንት ምሽት ፍሎሪዳን ስትመታ ፍጥነቷ 140 ኪ.ሜ. በሰዓት ነበር።
የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በጎርፍ የተጠቁ ሰዎችን ለማዳን በመረባረብ ላይ መሆናቸውም ተሰምቷል።
ከአውሎ ነፋሷ ጋራ በተገናኘ እስከ አሁን አራት ሰዎች እንደሞቱ የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።
ለአትላንታ ከተማ፣ ኽሊን ከ35 ዓመታት ወዲህ የተከሰተ ከባድ አውሎ ነፋስ መሆኗን የጆርጂያ ዩኒቨርስቲ የአየር ትንበያ ፕሮፌሰር ማርሻል ሸፐርድ አስታውቀዋል።
መድረክ / ፎረም