በዩናይትድ ስቴትስ የሰሜን ካሮላይና ባለስልጣናት ከባድ አውሎ ንፋስ በቀላቀለ ዝናብ ለተጠቁት የሀገሪቱ ደቡብ ምሥራቃዊ ግዛቶች ተጨማሪ የመጠጥ ውሃ እና ምግብ ለማዳረስ ቃል ገቡ፡፡
ኸሪኬንር ሔለን የተባለው ይኸው ከባድ ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ንፋስ በደቡብ ምሥራቃዊ የአሜሪካ ከተሞች ባደረሰው ጉዳት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 100 መድረሱ ተገልጿል፡፡ በተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች 91 ሰዎች ሲሞቱ በሰሜን ካሮላይና ብቻ ተራራማዋን አሽቪል ከተማ ጨምሮ 30 ሰዎች መሞታቸውን ተገልጿል፡፡ የሰሜን ካሮላይና ሀገረ ገዥ ሮይ ኩፐር የአደጋ ጊዜ እና የነፍስ አድን ሰራተኞች መሰረተ ልማቶች ወደ ወደሙባቸውን በፈራረሱ መንገዶች ምክንያት መድረስ ወዳልተቻለባቸው ስፍራዎች ሲደረስ፤ የሟቾቹ አሃዝ ሊያሻቅብ እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡ በመኪና ሊደረስባቸው ወዳልተቻሉ የአሽቪል አካባቢዎች እርዳታ በአየር እንዲዳረስ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የፈራረሱ መኖሪያ ቤቶችን እና ንብረቶችን መልሶ መገንባት ረዥም ጊዜ የሚፈጅ እና ከባድ መሆኑን ባለስልጣናቱ አስጠንቅቀዋል፡፡ አውሎ ንፋስ የቀላቀለው ዝናብ በደቡብ ምሥራቅ የሀገሪቱ ክፍል የብዙዎችን ሕይወት አመሰቃቅሏል፡፡ በፍሎሪዳ፣ ጆርጂያ፣ ደቡብ ካሮላይና እና ቨርጂኒያ ግዛቶች የሰዎች ህልፈት ተመዝግቧል፡፡
225 ኪሎሜትር በሰዓት የሚነጉደው ደረጃ አራት ዝናብ የቀላቀለው ከባድ አውሎ ንፋስ፤ ከትላንት እሁድ ማታ አንስቶ ሁለት ሚሊየን መኖሪያ ቤቶች የኃይል አቅርቦት ተቋርጦባቸዋል፡፡ በኃይል መቋረጥ በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዳቸው የደቡብ ካሮላይና ሀገረ ገዥ የሆኑት ሄነሪ ማክማስተር ሁኔታውን ለማስተካከል እየተሰራ በመሆኑ ዜጎች ትእግስት እንዲኖራቸው ጠይቀዋል፡፡
መድረክ / ፎረም