በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሀሪኬይን ሃርቪ ወደ ቴክሳስ ክፍለ ግዛት ጠረፍ አካባቢ እያመራ ነው


ከወደ ሜክሲኮ ባህረ ሰላጤ ከባድ ንፋስ ይዞት የሚነጉደው ከባድ ዝናብ ሀሪኬይን ሃርቪ ወደ ቴክሳስ ክፍለ ግዛት ጠረፍ አካባቢ እያመራ ነው።

ከወደ ሜክሲኮ ባህረ ሰላጤ ከባድ ንፋስ ይዞት የሚነጉደው ከባድ ዝናብ ሀሪኬይን ሃርቪ ወደ ቴክሳስ ክፍለ ግዛት ጠረፍ አካባቢ እያመራ ነው።

ባለሥልጣናት መጠነ ሰፊ ጥፋት ያስለክትላል ብለው ለሰጉበት ለዚህ ከባድ ንፋሳማ ዝናብ ውርጂብኝ እየተዘጋጁ ናቸው።

ዝናቡ ቴክሳስ የብሱ ላይ ከሰዓታት በኋላ ቢሆንም ፍጥነቱ ግን እየጨመረ ነው። በሰዓት ከሁለት መቶ ኪሎ ሜትር በሚበልጥ ፍጥነት የሚውዘገዘግ ንፋስ የሚነጉደው ዝናብ ጠረፉን አካባቢ ቢያንስ ሰማኒያ ሴንቲ ሜትር ያህል በውሃ ያጥለቀልቃል ተብሎ ተሰግቷል።

ሀሪኬይን ሃርቪ ቴክሳስ ላይ ከባድ ጉዳት እንደሚያደርስ የዩናይትድ ስቴትስ የፌዴራል አስቸኳይ ጉዳዮች አስተዳደር መሥሪያ ቤት ዋና ኃላፊ አስጠንቅቀዋል።

ዋናው ሥጋታቸው ማስጠንቀቂያውን ቸል ብለው ቤታቸውን ላለመልቀቅ የወሰኑ ጠረፉ አካባቢ የሚኖሩ አንዳንድ ዜጎች መኖራቸው ነው ብለዋል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG