በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፕሬዝደንቱ ልጅ በፍ/ቤት ጥፋተኛ ተባሉ


የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ልጅ የሆኑት ሃንተር ባይደን
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ልጅ የሆኑት ሃንተር ባይደን

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ልጅ የሆኑት ሃንተር ባይደን የአደንዛዥ ዕጽ ተጠቃሚዎች መሣሪያ እንዳይገዙ እና እንዳይታጠቁ የሚከለክለውን ሕግ ጥሰዋል በሚል በቀረቡባቸው ሶስት የክስ ዓይነቶች ጥፋተኛ ተብለዋል።

ሃንተር ባይደን በእ.አ.አ 2018 ፈቃድ ካለው መሣሪያ ሻጭ ግብይት በፈፀሙበት ወቅት በሞሉት ፎርም ላይ “የአደንዛዥ ዕጽ ተጠቃሚ አለመሆናቸውን በመዋሸት አመልክተዋል፣ መሣሪያውንም ለ 11 ቀናት ይዘዋል” በሚል ክስ የቀረበባቸው ሲሆን፣ ትላንት ማክሰኞ ጥፋተኛ ተብለዋል።

የአደንዛዥ ዕጽ ተጠቃሚ አለመሆናቸውን በመዋሸት አመልክተዋል፣ መሣሪያውንም ለ 11 ቀናት ይዘዋል”

ወንጀሉ እስከ 25 ዓመት የሚያስቀጣ ሲሆን፣ ወንጀሉን የፈጸሙት ለመጀመሪያ ጊዜ በመሆኑ 25 ዓመት ላይፈረድባቸው እንደሚችል ተመልክቷል። ዳኛዋ ማርሊን ኖሪየካ ቅጣቱን የሚያሰሙበትን ቀን ያላሳወቁ ሲሆን፣ ሃንተር ባይደንን ወደ ዘብ ጥያ ይልኩ እንደሆነም ለጊዜው አልታወቀም።

ሃንተር ባይደን መሣሪያውን በገዙበት ወቅት ከሱስ ለመውጣት የሚያስፈልገውን ፕሮግራም ማጠናቀቃቸውን ለፍ/ቤት የገለጹት ጠበቆቻቸው፣ ከሱስ ለመውጣትና ሕይወታቸውን ለማስተካከል በመጣር ላይ እንደነበሩ አስረድተዋል።

ፕሬዝደንት ባይደን የጥፋተኝነት ፍርዱ ከተሰማ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት የፍርድ ሂደቱንም እንደሚያከብሩ አስታውቀዋል።

ሃንተር ባይደንና ጠበቆቻቸው ይግባኝ እንድሚጠይቁ አስታውቀዋል።

ሃንተር ባይደን ጥፋቱን የፈጸሙት ጆ ባይደን ፕሬዝደንት ከመሆናቸው በፊት ቢሆንም፣ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ የተባሉ የመጀመሪያው የፕሬዝደንት ቤተሰብ ሆነዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG