በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“በትግራይ 1ሺ99 የሚደርሱ ህጻናት በምግብ እጥረት ሞተዋል” ተባለ


ፎቶ ፋይል፦ መቀሌ
ፎቶ ፋይል፦ መቀሌ

ጦርነት ውስጥ ባለችው ትግራይ፣ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ፣ ቢያንስ 1ሺ900 የሚደርሱ ህጻናት በተመጣጠነ የምግብ እጥረት መሞታቸውን በክልሉ ጤና ባለሥልጣናት የተሰናዳውን ጥናት መሰረት ያደረገው የአሶሼይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

ጥናቱ፣ እኤአ ካለፈው ዓመት ሰኔ እስከ ዘንድሮ ሚያዝያ 1 ድረስ፣ በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ የተመለከተ መሆኑን ተዘግቧል፡፡ ጥናቱ አሁን በአማራክልል ቁጥጥር ስር የሚገኘውንና ምዕራብ ትግራይ የተባለውን አካባቢ የማያካትት መሆኑን የአሶሼይትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

በጥናቱ የተሳተፉት አንድ ሀኪም ብዙዎቹ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ጤና ማዕከላቱ ሊያመጡ ባለመቻላቸው፣ በምግብ እጥረቱ የሞቱት ህጻናት ቁጥር በጥናቱ ከተጠቀሰው በላይ ሊሆኑ እንደሚችል አስታውቀዋል፡፡

በትግራይ ከሚገኘው 5.5 ሚሊዮን ህዝብ 90 ከመቶ የሚሆነው እርዳታ የሚፈልግ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 115ሺ የሚሆኑት በከፍተኛ የምግብ እጥረት ስር የሚገኙ መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት ያመለክታል፡፡

XS
SM
MD
LG