በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሃንጋሪ ለዩክሬን የታቀደውን የአውሮፓ ኅብረት የገንዘብ ርዳታ አገደች


የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርልስ ሚሼል፣ ዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ እና የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደ ሌይን በአውሮፓ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ
የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርልስ ሚሼል፣ ዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ እና የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደ ሌይን በአውሮፓ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ

ሃንጋሪ፣ የአውሮፓ ኅብረት ለዩክሬን ድጋፍ ያቀደው የገንዘብ ርዳታ እንዳይሰጥ፣ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብቷን ተጠቅማ አገደች።

ርዳታው ለዩክሬን እንዳይሰጥ፣ ዛሬ ዐርብ፣ ድምፅን በድምፅ የመሻር ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ያገዱት፣ የሃንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን ናቸው።

የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርልስ ሚሼል ግን፣ ከኻያ ሰባቱ የኅብረቱ አባል ሀገራት ውስጥ ኻያ ስድስቱ፣ የ54 ቢሊዮን ዶላር ድጋፉ፣ ዩክሬን በሩሲያ የተቃጣባትን ወረራ ለመቋቋም በእጅጉ እንደሚያስፈልጋትና እንዲሰጣትም መፍቀዳቸውን አስታውቀዋል።

ስዊድን በበኩሏ፣ ርዳታውን አስመልክቶ በተለመደው አሠራሯ፣ የአገሪቱን ብሔራዊ ሸንጎ ማማከር እንዳለባት፣ የአህጉራዊው ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል፣ አህጉራዊው ኅብረት፣ በጦርነት የተጠመደችውን ዩክሬንን በአባልነት በመቀበል ጉዳይ ላይ ንግግር እንዲጀመር፣ ትላንት ኀሙስ ከስምምነት ላይ ደርሷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG