በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጋዛውን ጦርነት የተቃውሙ የሃርቫድ ምሩቃን ስነስርዓቱን አቋርጠው ወጡ

የመመረቂያ ልብሶቻቸውን የለበሱ በመቶዎች የሚቆጠሩ የሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የጋዛውን ጦርነት በመቃወም ትላንት ሐሙስ የተካሄደውን የምርቃት ስነስርዓት አቋርጠው ወጡ፡፡

ተማሪዎቹ የወጡት “ነጻነት! ነጻነት ለፍልስጤም!”፣ የመሳሰሉትን መፈክሮችን እያሰሙ ነበር፡፡ የሐሙሱ ክስተት የታየው በዩኒቨርስቲ ግቢዎች ለሳምንታት ከዘለቀው ተቃውሞ በኋላ ነው፡፡

የትምህርት ቤቱ ኃላፊዎች ከምረቃው ስነሥርዓት አንድ ቀን በፊት ከትላንት በስቲያ ረቡዕ እንዳስታወቁት፣ ድንኳን በመትከል ግቢ ውስጥ በነበረው ተቃውሞው የተሳተፉ 13 የሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ከክፍል ጓደኞቻቸው ጋር ተሰልፈው ዲግሪያቸውን አዳራሽ ውስጥ መቀበል አይችሉም።

አንዳንድ ተማሪዎች የተከለከሉትን ተማሪዎች በመጥቀስ አብረውን “እንዲወስዱ ፍቀዱላቸው!” ሲሉ በህብረት ባሰሙት ጩኸት ጠይቀዋል፡፡

የተማሪዎችን የወከለችው ተናጋሪ 13ቱን ተማሪዎችን በመጥቀስ በግቢው ውስጥ የመናገር ነፃነት፣ የሕዝባዊ እምቢተኝነት መብት እና መቻቻል አለመኖሩ በእጅጉ እንዳሳዘናት ተናግራለች።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG