በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለሌሶቶ ረሃብ ተመድ ሠላሳ አራት ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ተማጸነ


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሌሶቶ በከባድ ረሃብ ላይ ለሚገኘው ሩብ ሚሊዮን በላይ ህዝብ በሚቀጥሉት አራት ወራት ህይወት አድን ዕርዳታ የሚያቅርብበት ሠላሳ አራት ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ተማጸነ።

የሌሶቶ ህዝብ የሚበዛው በግብርና የሚተዳደር ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ሃገሪቱ በከባድ ድርቅ ተመታትለች። በድርቁ ምክንያት ሰብል ባለመገኘቱ የብዙ ህዝብ ህይወት ለአደጋ እንደተጋለጠ ነው የተመዱ ሪፖርት ያመለከተው። ሰባ አንድ ሺህ ህዝብ የከበደ ቸነፈር አፋፍ ላይ እንደሆንም የመንግሥታቱ ድርጅት አስታውቋል።

የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ቢሮ ኦቻ ቃል አቀባይ ዬይንስ ላርኪ ያቀረብነው የዕርዳታ ተማጽኖ በዚህ አስጊ ወቅት ድርቁ ከጎዳው ህዝብ ግማሽ የሚሆኑት ህይወት ለመታደግ ነው ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG