በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍልስጤማውያን በሐማሱ መሪ ቀብር ላይ ተገኙ


ሳሊህ አል-አሩሪ ቀብር ላይ ከአንድ ሺ በላይ የሚሆኑ ሐዘንተኞች መገኘታቸው ተነገረ፡፡
ሳሊህ አል-አሩሪ ቀብር ላይ ከአንድ ሺ በላይ የሚሆኑ ሐዘንተኞች መገኘታቸው ተነገረ፡፡

ሊባኖስ ውስጥ ባላፈው ማክሰኞ በእስራኤል እንደተገደሉ በተነገረው የሐማስ ሁለኛው ሰው ሳሊህ አል-አሩሪ ቀብር ላይ ከአንድ ሺ በላይ የሚሆኑ ሐዘንተኞች መገኘታቸው ተነገረ፡፡

ሐዘንተኞቹ ሐማስ አል አሩሪ እና አብረዋቸው የሞቱትን ሌሎች አምስት የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን አባላትን ሞት እንዲበቀል ጠይቀዋል፡፡

አሩሪ እና ሌሎች የሃማስ አባላት የተገደሉት ደቡብ ቤይሩት ውስጥ በኢራን የሚደገፈው ታጣቂው ሄዝቦላህ ይዞታ ውስጥ ነው።

የሐማስ እና የሊባኖስ የደህንነት ባለሥልጣናት ጥቃቱን የፈፀመችው እስራኤል ናት ሲሉ አንድ የሊባኖስ የደህንነት ከፍተኛ ባለስልጣን ተጎጂዎቹ ከሌላ ቦታ በተመሩ ሚሳዬሎች ዒላማ መሆናቸውን ተናግረዋል።

አንድ የአሜሪካ የመከላከያ ባለሥልጣን ለኤኤፍፒ ባላፈው ረቡዕ እንደገለፁት ከጥቃቱ ጀርባ እስራኤል አለችበት ብለዋል፡፡

እስራኤል ኃላፊነቱን አልወሰደችም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG