በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሑመራና የዳንሻ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ


ሑመራ
ሑመራ

ከጦርነቱ ማግስት ጀምሮ “ማንነትን የለየ ትንኮሳ እና የንብረት ዘረፋ በሑመራ ከተማና ጦርነቱ በነበረባቸው ከተሞች እየተፈፀመ ነው” ሲሉ አንዳንድ የከተማዪቱ ነዋሪ የትግራይ ብሄር ተወላጆች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

አብዛኛዎቹ ወንዶች እና ወጣቶች የሆኑ የትግራይ ብሄር አባላት ከተማዋን ለቅቀው ወደ ሱዳን መሰደዳቸውንና ወደ ማዕከላዊ ትግራይ መሄዳቸውን ገልፀው ከጦርነቱ መልስ ለቤተቤተሰባዊና ማኅበራዊ ቀውስ እንዲሁም ለረሃብ እንደተጋለጡ ገልጸዋል።

“በህወሓት ሲፈፀሙ የነበሩ ስህተት አሁንም እየተደገሙ ናቸው” ሲሉ ሪፖርተራችን ያነጋገራቸው የዳንሻ ከተማ ነዋሪዎች ስሞታ አሰምተዋል።

የሑመራ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር የሰላምና ደህንነት ዘርፍ አስተባባሪ መከላከያ ሠራዊቱ እና የአማራ ልዩ ኃይል ከተማውን ከተቆጣጠሩ በኋላ የዘረፋ ወንጀል መቆሙን ገልጸው መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት ለመጠበቅ እየሠራ እንደሆነ አመልክተዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የሑመራና የዳንሻ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:13 0:00


XS
SM
MD
LG