በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሂዩማን ራይትስ ዋች ሪፖርት በአፍሪካ ጉዳይ


ባለፈው ወር ባበቃው ዓመት በአፍሪካ ዙርያ ቁጣና ተቃውሞ ሰፍኖ እንደነበርና አሁንም ሲቀዘቅዝ አለመታየቱን ሂዩማን ራይትስ ዋች የተባለው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ያወጣው ዓመታዊ ዘገባ ገምግሟል።

ጊኒና ሱዳን ውስጥ ለረዥም ጊዜ ሲገዙ በቆዩ መሪዎች ላይ ቁጣ ታይቷል። የዚምባብዌ ኢኮኖሚ መዳሸቅ ተቃውሞ አስነስቷል። በኮንጎ ዲሞክራስያዊ ሪፖብሊክና በኢትዮጵያ ግጭቶችና ከመኖርያ የመፈናቀል ሁኔታ ተከስቷል።

በኮናክሪ፣ ሀራሬ፣ ኻርቱምና ኪንሻሳ ተቃውሞ የተካሄደባቸው ምክንያቶች ቢለያዩም ከፀጥታ ኃይሎች የገጠማቸው ከባድ ምላሽ ተመሳሳይ ነበር ይላል ሂዩማን ራይትስ ዋች ያወጣው ዘገባ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG