በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሂዩማን ራይትስ ዋች ሪፖርት

ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የኢራቅና የኩርድ ባለሥልጣናት እስላማዊ መንግሥት ነኝ ከሚለው ጽንፈኛ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው የሚሏቸውን በመቶዎች የሚቆጠሩ ልጆች አሥረዋል፣ ሰቆቃ ይፈጸምባቸዋል ሲል ሂዩማን ራይትስ ዋች የተባለው ዓለምቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት አዲስ ባወጣው ሪፖርት ገለጸ።

የኢራቅና የኩርድ ባለሥልጣናት እስላማዊ መንግሥት ነኝ ከሚለው ጽንፈኛ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው የሚሏቸውን በመቶዎች የሚቆጠሩ ልጆች አሥረዋል፣ ሰቆቃ ይፈጸምባቸዋል ሲል ሂዩማን ራይትስ ዋች የተባለው ዓለምቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት አዲስ ባወጣው ሪፖርት ገለጸ።

የ14 ዓመት እድሜ ያላቸው ሕፃናት ሳይቀሩ የድርጊቱ ሰለባዎች መሆናቸውንም አመልክቷል።

ሪፖርቱ እንደሚለው እአአ በ2018 ማብቂያ ላይ የኢራቅና የኩርድ መንግሥታት ከእስላማዊ መንግሥት ቡድን ጋር ተባብረዋል ያሏቸውን 1,500 የሚሆኑ ሕጻናት አስረው ነበር።

ሂዩማን ራይትስ ዋች ካሸባሪዎች ጋር በመተባበር ተከሰው በእሥር ላይ የቆዩ በርካታ ወንድ ልጆችን አነጋግሯል።

አንደኛው ልጅ ሲያስረዳ የታሰርኩት ሞሱል ውስጥ አሸባሪዎች ያዘወትሩት በነበረ አንድ ምግብ ቤት በመሥራቴ ነው ብሏል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG