በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም የሰብዓዊ መብቶች ሪፖርት


በተጠናቀቀው የአውሮፓ 2016 ዓ.ም ለዓለም የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ከፍተኛውን አደጋ የደቀነው “እያንሠራራ የመጣው ርካሽ የሚባል የሕዝብ ተቀባይነትን የማግኘት አዝማሚያ ነው” ሲል ሂዩማን ራይትስ ዋች የሚባለው የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን አስታወቀ፡፡

ይህ ትናንት ዋሺንግተን ዲሲ ላይ የወጣ የ2017 ዓ.ም የዓለም የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ሪፖርት በዩናይትድ ስቴትስና በሌሎችም ሀገሮች ውስጥ የተካሄዱ ምርጫዎች፣ የስደት ቀውስ እና የአምባገነኖች ማንሠራራት በሰብዓዊ መብቶች ላይ የነበሯቸውን አንድምታዎች ጠቅሷል፡፡

687 ገፆች ያሉት ይህ ሪፖርት የዘጠና ሃገሮችን የመብቶች አያያዝ የፈተሸ ሲሆን ይህ ጊዜ በተለየ ሁኔታ አሳሳቢ ነው ሲሉ የሂዩማን ራይትስ ዋች ዋና ዳይሬክተር ኬኔት ሮዝ ሥጋታቸውን ገልፀዋል፡፡

ጠባብ አካባቢያዊነት፣ መጤ-ጠልነት፣ ዘረኝነት፣ እሥልምናን መጥላት፣ ሴትን ማተነስ የመሳሰሉ ችግሮች እያንሠራሩ መሆናቸውን የተናገሩት ሮዝ ያለመቻቻል አዝማሚያዎችና አድራጎቶች እየበረቱ በሄዱ መጠን ዓለም ወደ ጭለማ ዘመን የመግባት ሥጋት እንደሚፀናበት አስጠንቅቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG