በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለአደጋ ከተጋለጡ ሕዝቦች ስድስቱ የሚገኙት በአፍሪቃ መሆኑ ተገለፀ


ዋና ቢሮው ሎንዶን ውስጥ የሆነው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን፣ ስድስቱ አገሮች ሶማልያ፣ ሱዳን፣ ኰንጎ ዲሞክራቲክ ሬፐብሊክ፣ ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያና አይቮሪ-ኮስት መሆናቸውን አመለከተ

ቡድኑ በዘንድሮ ዘገባው፣ «ለአደጋ የተጋለጡ ሕዝቦች» ዝርዝሩ ውስጥ በቀዳሚነት ያስቀመጠው፣ በጦርነት የምትታመሰዋንና የባንቱ አናሳ ቡድን ተለይቶ ለአደጋ የተጋለጠባትን ሶማልያን ነው።

ሞሓመድ ሀሰን ዳሪየል የአናሳን ሶማሌዎች የሰብዓዊ መብት አስጠባቂ ፎረም ኃላፊ ናቸው። በግብርና ሥራ የነሰማሩትና ተክለ-ሰወታቸውም ልዩ የሆኑት ባንቱዎች፣ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ነው የሚታዩት ይላሉ። «በማኅበራዊ ኑሯቸው ጭቁን የኅበረተሰብ ክፍሎች ሲሆኑ ጎሣዎቻቸውም ከእኛ የተለዩ ናቸው። ሶማሌዎች ጥንት እንደ ባርያ ነበር የሚቆጥሯቸው» ብለዋል።

በዝርዝሩ፣ ፪ኛ ተራ ላይ ያለችው፣ በቅርቡ በተካሄደ ውሳኔ-ሕዝብ መሠረት ወደ ሁለት አገር ወደመሆን ሂደት ላይ የምትገኘው ሱዳን ነች። በሪፖርቱ መሠረት፣ ደቡብ ሱዳንና ዳርፉር ውስጥ የሚገኙ ማህበረሰቦች፣ ለከፍተኛ አደጋ የተጋለጡ ናቸው።

ማሩስካ ፔራዚ የዓለማቀፉ፣ አናሳ ቁጥር ያላቸው ሕዝቦች መብት አስጠባቂ ቡድን ቃል-አቀባይ ናቸው። እርሳቸው እንደሚሉት፣ በውሳኔ-ሕዝቡ መሠረት ደቡብና ሰሜን በመባል የሚካሄደው ክፍፍል ብቻ አይደለም፣ እንደ ዲንካና ኑዌር የመሰሉትን ከብት አርቢዎች የሚጎዳቸው። እሳቸው እንደተናገሩት፣ ከፖለቲካው የበለጡ፣ ሌሎች በርካታ ጉዳዮች አሉ።

በአገሪቱ በሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶች፣ በነዚሁ በተለይም በደቡቡ ክፍል በሚገኝ የኤክኖሚ ጥቅም የተነሳ በማህበረሰቦቹ መካከል የሚካሄደው ጦርነትም እንደ ዋነኛ መንሥዔ ሊቆጠር ይችላል።

ሙሉውን ዘገባ ያዳምጡ፡

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG