ዋሺንግተን ዲሲ —
ጠቅላላው የሰብዓዊ መብቶች አጠባበቅ ሥርዓት በሽብርተኛነት፣ በመጤ ጠሎችና ዝናን ናፋቂ በሆኑ ፖለቲከኞች፣ ከፍተኛ ጥቃት ሥር ወድቋል ሲሉ፣ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ዘይድ ራአድ አል ሁሴን አስገንዝበዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሺነር ዘይድ ራአድ አል ሁሴን በሪፖርታቸው በአሁኑ ወቅት ከአርባ ሀገሮች በላይ የሚታየውን የመብት ይዞታ ዘርዝረዋል፡፡
ከእነዚህ መካከል አራቱን ሀገሮች ጋምቢያ፣ ኡዝቤክስታን፣ ቱኒዚያ እና ግሪክን ጠቅሰዋል፡፡
ከፍተኛ ኮሚሸነሩ ዓመታዊ ሪፖርታችውን ካቀረቡበት የመሥሪያ ቤቱ ጠቅላይ ቢሮ ከሚገኝበት ጄኔቫ ሊሳ ሽላይን ያጠናቀረችውን ዘገባ አዲሱ አበበ ያቀርበዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ