በአዲስ አበባ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራትንና ከአፍሪካ ውጭም የሌሎች ሀገራት ዲዛይነሮችን ያሳተፈ የፋሽን ትርዒት ተካሒዷል፡፡ “ሀብ ኦፍ አፍሪካ ፋሽን ዊክ” በሚባል ተቋም የተዘጋጀው ይኸው ለአምስት ቀናት የቆየው የፋሽን ትርኢት፣ 18 ዲዛይነሮች የፈጠራ ስራዎቻቸውን አሳይተውበታል፣ ተመልካቾችንም አዝናንተውበታል፡፡ አዘጋጆቹ፣
የፋሽን ትርዒቱ አዳዲስ የአልባሳት ዲዛይኖችን ለማስተዋወቅ ዕድል ይፈጥራል ሲሉ፣ ዲዛይነሮቹ ደግሞ የገበያ ትስስር የሚፈጠርበትና ልምድ የሚለዋወጡበት መድረክ መሆኑን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡
መድረክ / ፎረም