በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ደ ክለርክ አረፉ


ፎቶ ፋይል፦ የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ደ ክለርክ፤ የደቡብ አፍሪካ ጥቁር ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ
ፎቶ ፋይል፦ የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ደ ክለርክ፤ የደቡብ አፍሪካ ጥቁር ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ

የደቡብ አፍሪካ የመጨረሻው የአፓርታይድ ዘመን ፕሬዚዳንት ኤፍ ደብሊው ደ ክለርክ አረፉ።

እአአ በ1993 ከመጀመሪያው የደቡብ አፍሪካ ጥቁር ፕሬዚዳንት ከኔልሰን ማንዴላ ጋር በጋራ የኖቤል የሰላም የተሸለሙት ደ ክለርክ በሰማኒያ አምስት ዓመታቸው ኬፕታውን አቅራቢያ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ሚሶቶሊዮማ በሚባለው የሳምባ ካንሰር ሳቢያ ህይወታቸው ማለፉን የደ ክለርክ የበጎ አድራጎት ተቋም ባወጣው መግለጫ ዛሬ አረጋግጧል።

እአአ በ1990 በፕሬዚዳንትነት በተሰየሙ በአምስተኛ ወራቸው በወቅቱ፣ የበርሊን ግንብ ከፈረሰ ገና ሦስት ወር አልሞላው ነበር። በሀገራቸው ከአርባ ዓመታት በላይ የዘለቀውን የአፓርታይድ ስርዓት የሚያከትም ዓለምን ያስገረመ እርምጃ መውሰዳቸው ይታወሳል።

“በአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ፓርቲ ላይ በህገ ወጥነት ተፈርጆ የተጣለበት ዕገዳ ይነሳል። መሪው ኔልሰን ማንዴላም ይለቀቃሉ" በማለት በደቡብ አፍሪካ ፓርላማ ዱብ እዳውን ንግግር ባደረጉ በዘጠነኛው ቀን ለሃያ ሰባት ዓመታት እስር ላይ የቆዩት ኔልሰን ማንዴላ ተለቀቁ።

ይህ በሆነ በአራተኛው ዓመት በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁሉም ዘሮች የተካፈሉበት ብሄራዊ ምርጫ ማንዴላ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ። ማንዴላ እና ደ ክለርክ ስላደረጉት ትብብር እአአ በ1993 በጋራ የኖቤል የሰላም ሽልማት ማሸነፋቸው ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG