በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአሜሪካ በመጠጥ ውሃ ውስጥ በሚገኙ ኬሚካሎች መጠን ላይ ገደብ ተጣለ


 ፎቶ ፋይል፦ የውሃ ናሙና ለምርመራ ሲዘጋጅ እአአ የካቲት 16/2023
ፎቶ ፋይል፦ የውሃ ናሙና ለምርመራ ሲዘጋጅ እአአ የካቲት 16/2023

በአሜሪካ በመጠጥ ውሃ ውስጥ የሚገኙ መርዛማ ኬሚካሎችን መጠን የሚገድብ ደንብ የባይደን አስተዳደር አውጥቷል።

የውሃ አቅራቢ ኩባንያዎች የኬሚካሎቹን መጠን በሚቻለው ዝቅተኛ እንዲያደርጉና ይህም መለካት እንዳለበት ደንቡ አመልክቷል።

በመጠጥ ውሃ ላይ ለመጀመሪያ ግዜ የተጣለ የኬሚካል መጠን ገደብ እንደሆነ የተገለፀው እርምጃ፣ መቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከአደገኛ ኬሚካል እንዲጠበቁ የሚያደርግና፣ ካንሰርን ጨምሮ በሺሕ የሚቆጠሩ በሽታዎችን መከላከል የሚያስችል ነው ተብሏል።

የጤና ጥበቃ አቀንቃኖች የአካባቢ ጥበቃ መ/ቤቱ ደንቡን ለማስፈጸም ያደረገውን ጥረት ሲያደንቁ፣ የውሃ አቅራቢ ኩባንያዎች ግን፣ ኬሚካሎቹን በተባለው መጠን ለማፅዳት ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ደንበኞች ተጨማሪ ለመክፈል ይገደዳሉ ብለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG