በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
በማኅበራዊ ሚዲያ የወጡ ምስሎች በሱዳን የጦር ወንጀል መፈጸማቸውን ያመለክታሉ - ሂዩማን ራይትስ ዋች

በማኅበራዊ ሚዲያ የወጡ ምስሎች በሱዳን የጦር ወንጀል መፈጸማቸውን ያመለክታሉ - ሂዩማን ራይትስ ዋች


የጅምላ ግድያ፣ ማሰቃየት እና አስከሬንን መቆራረጥ ጨምሮ ሌሎችንም የጦር ወንጀሎች በሱዳን ሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች ፈጽመዋል ሲል የሰብዓዊ መብት ድርጅቱ ሂውማን ራይትስ ዋች ዛሬ ሐሙስ አስታውቋል።

መሠረቱን በኒው ዮርክ ያደረገው የመብት ድርጅት፣ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚወጡ ምስሎችን መመርመሩን እና ቢያንስ 40 የሚሆኑ ሰዎች በጅምላ መገደላቸውን እንዲሁም 18 የሚሆኑ ታጋቾች ደግሞ ስቃይና አጉል አያያዝ እንድተፈጸመባቸው አስታውቋል።

ሃያ የሚሆኑ ቪዲዮዎችን መርምሬያለሁ ያለው ሂዩማን ራይትስ ዋች፣ በዘጠኙ ቪዲዮዎች ላይ ቢያንስ ስምንት የሚሆኑ አስከሬኖች በአብዛኛው ወታደራዊ መለዮ በለበሱ ሰዎች ሲቆራረጡ አመልክተዋል ብሏል።

በአብዛኛው ታጋቾቹ መሣሪያ ያልታጠቁ፣ ስጋት የማይፈጥሩ እና እጅ እግራቸው የታሰረ እንደሆነ መታዘቡንም ድርጅቱ አመልክቷል።

“በሱዳን በሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች ውስጥ ያሉ ኃይሎች ሲገድሉ፤ ሲያሰቃዩ፣ አስክከሬን ሲቆራርጡ በካሜራ መቅረጻቸው፣ ተጠያቂነት እና ቅጣት እንደማይኖር የተሰማቸው ይመስላል” ብለዋል በሱዳን የድርጅቱ ወኪል ሞሃመድ ኦስማን።

“ወንጀሎቹ እንደ ጦር ወንጀል መመርመርና የኃይሎቹ አዛዦችን ጨምሮ ድርጊቱን የፈጸሙት ሁሉ ተጠያቂ መሆን አለባቸው” ሲሉ አክለዋል ሞሃመድ ኦስማን።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG