በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሂዩማን ራይትስ ዋች ሱዳን ላይ ጠንካራ የጦር መሣሪያ ማዕቀብ እንዲጣል ጠየቀ


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ወደ ሱዳን ምዕራብ ዳርፉር ግዛት የጦር መሣሪያ መላክን የሚከለክለው ማዕቀብ፤ መታደስ አለመታደስ ላይ ነገ ረቡዕ ድምጽ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቋሙ ሂዩማን ራይትስ ዋች ከነገው ድምጽ አሰጣጥ ቀደም ብሎ የጸጥታ ምክር ቤቱ በምዕራብ ዳርፉር ላይ የሚያተኩረውን የጦር መሣሪያ ማዕቀብ ሰፋ በማድረግ በመላ ሱዳን ሥራ ላይ እንዲያውለው አሳስቧል። የሱዳን መንግሥት ዕገዳውን ይቃወማል።

ሂዩማን ራይትስ ዋች ያወጣቸው ዘገባዎች ከተተኮሱት ሞርታሮች መካከል አንዳንዶቹ ባለፈው ዓመት በቻይና እንደተመረቱ ሲያመላክት፤ የተወሰኑት ደግሞ የኢራን፣ ሩሲያ፣ ሰርቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የሚገኙ ኩባንያዎችም የተመረቱ የጦር መሣሪያዎች መሆናቸውን አመላክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG