በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመብቶች ተሟጋቹ አዲስ ጥያቄ ለኢትዮጵያ መንግሥት


የኢትዮጵያ መንግሥት በፀረ-ሽብር ሕጉ ጋዜጠኞችንና በፖለቲካው ውስጥ የሚንቀሣቀሱ ሰዎችን ማሰር እንዲያቆም ሁለት ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድኖች ጠየቁ፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ በሕይወት ካሉት የመጨረሻዎቹ ነፃ ጋዜጦች የአንዱ አዘጋጅ ሌሎች እሥራቶች ይከተላሉ በሚል ሥጋት ከሃገር ወጥቷል፡፡

ሂዩማን ራይትስ ዋች እና አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባልተለመደ ሁኔታ መግለጫውን በጋራ ያወጡት አሥር ጋዜጠኞች በሽብር ፈጠራ ተከስሰው ጉዳያቸው በሦስት የተለያዩ ችሎቶች ላይ እየታየ ባለበት ወቅት ነው፡፡

ከችሎቶቹ በአንደኛው ላይ የቀረቡት የተለያዩ ተቃዋሚዎችን ጨምሮ የተከሰሱ 24 ሰዎች ናቸው፡፡

“የኢትዮጵያ ፀረ-ሽብር ሕግ የተድበሰበሰና ለፖለቲካ ጥቅም ለማዋል ክፍት በመሆኑ አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና የእርሣቸው ቡድን ሂዩማን ራይትስ ዋች በአንድ ድምፅ ለመናገር ወስነዋል” ብለዋል መርማሪው ቤን ሮውለንስ ለቪኦኤ በስልክ በሰጡት መግለጫ፡፡

የቡድኖቹ መግለጫ የወጣው በኢትዮጵያ እጅግ ተነባቢ ነው የሚባለው የግል ጋዜጣ መዘጋቱና አዘጋጁ ዳዊት ከበደም “እታሠራለሁ” በሚል ሥጋት ሃገር ጥሎ መውጣቱ እየተነገረ ባለበት ወቅት ነው፡፡

ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG