በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሃያ አንደኛው የሰብዓዊ መብቶች ሪፖርት


ዓለምአቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች ምዕራባዊያን በተለይም የአውሮፓ ኅብረት መንግሥታት፣ መብት ረጋጭ መንግሥታት ከድርጊታቸው እንዲታረሙ ጫና አያደርጉም ሲል ወቀሰ።

ዓለምአቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች ምዕራባዊያን በተለይም የአውሮፓ ኅብረት መንግሥታት፣ መብት ረጋጭ መንግሥታት ከድርጊታቸው እንዲታረሙ ጫና አያደርጉም ሲል ወቀሰ።

ሂዩማን ራይትስ ዋች በ21ኛው ዓመታዊ ሪፓርቱ ዴሞክራሲያዊ መርህ የሚያራምዱ ምዕራባዊያን አገሮች በፖለቲካና በኢኮኖሚ ምክንያት ሌሎች አገሮች ላይ ያላቸው ተጽዕኖ በመሸርሸሩ መብት የሚጥሱትን ለመገሰፅ ድፍረቱ የላቸውም ብሏል።

ሪፓርቱ ዴሞክራሲን አላስከብር አሉ ያላቸውን እንደ ተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ባን ኪሙን ፥ እንደ አውሮፓ ኅብረት የውጭ ፖሊሲ ኃላፊ ኬትሪን አሽተን እና እንደ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ያሉትን በስም ይጠቅሳል።

"ሰብአዊ መብቶችን የማስከበር ልምድ ያላቸውና ሲጣስም እርምጃ የሚወስዱ አሁን ችላ ማለትን መምረጣቸው አዲሱ የዓለም ሥርዓት መሆኑ አሳሳቢ ነው" ይላል ሪፖርቱ።

"እራሣቸው ዴሞክራሲያዊ የሆኑ አገሮችም ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ ከባድ የመብት ጥሰት ውስጥ ስለገቡ ተጠያቂ ሆነዋል፡፡ ለዴሞክራሲ ለመቆም ድፍረት እያነሣቸው መምጣቱም ለሰብአዊ መብቶች ጥበቃ መላላት አንዱ ምክንያት ነው" ይላል።

በዩናይትድ ስቴትስ እና በአውሮፓ አገሮች የሚወሰድ ፀረ ሽብር እርምጃ ሰብአዊ መብቶች እንዲጣሱ አድርጓል። በአውሮፓ በተለይ አናሣ ቁጥር ባላቸው ዜጎች ላይ አድሎው እየጨመረ ሄዷል። ባለፈው ዓመት በርካታ የአውሮፓ አገሮች ሮማ ወይም ጂፕሲ የሚባሉ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ በሚኖሩ ሰዎች ላይ እርምጃ ሲወስዱ እንደነበርና የሰብአዊ መብት ቡድኖች እርምጃውን በመቃወም ድምፃቸውን ማሰማታቸው ተመልክቷል።

የስብአዊ መብቶች ተሟጋቹ ሂዩማን ራይትስ ዋች "ኢራን፣ ሚያንማር፣ ሰሜን ኮሪያ፣ የመን፣ ዚምባብዌ ክፉኛ መብት ረጋጭ የሆኑ መንግሥታት ናቸው" ብሏል። በቻይና ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣ ይካሄዳል፥ ሆኖም ምዕራባዊያን መንግሥታት ይህ እንዲለወጥ ብዙም አይገፉም። ምክንያትም ቻይና አሁን በዓለም ከፍተኛ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ተዋናይ ስለሆነች ስለምትፈፀመው ብርቱ የሰብአዊ መብቶች ረገጣ ለማንሣት ምዕራባዊያን ድፍረቱ ጎድሏቸዋል።

"በአፍሪቃ ኢትዮጵያና ርዋንዳ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ህዝባዊ አፈና እየከበደባቸው መጥቷል፡፡ ምዕራባዊያን ግን እነዚህን አገሮች ከሚያስተዳደሩ መንግሥታት ጋር ቅርበት ስላላቸው እያዩ እንዳላዩ መሆንን መርጠዋል ይላል ሪፖርቱ። ዝርዝሩን ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG