በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በUS ምክር ቤት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ረቂቅ ሕግ ቀጣይ እጣ እና ሌሎች ቁልፍ ጉዳዮች


Congressman Mike Coffman
Congressman Mike Coffman
በUS ምክር ቤት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ረቂቅ ሕግ ቀጣይ እጣ እና ...
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:37 0:00

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ ግፊት ለማድረግ በሚል ባለፈው ዓመት በየካቲት ወር መጀመሪያ ለዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የቀረበ ረቂቅ ሕግ ቀጣይ ሂደት ዙሪያ የተካሄደ ጋዜጣዊ ጉባኤ ነው የቀጣዩ ዘገባ መነሻ።

ባሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የሚታየው ሁኔታ ካልተለወጠ HR-128 የሚል መጠሪያ የተሰጠው ይህ ረቂቅ ሕግ ወደ ሙሉ ምክር ቤቱ የሚተላለፍና ሊጸድቅ የሚችል መሆኑ ነው፤ በምክር ቤቱ የብዙኃኑ ፓርቲ ተጠሪ በተገኙበት በተካሄደው ጋዜጣዊ ጉባኤ የተገለጸው።

በኢትዮጵያ ተፈጽመዋልና እየተፈጸሙ ናቸው የሚላቸውን የመብት ጥሰቶች የሚያወግዘው ባለፈው ዓመት በየካቲት ወር መጀመሪያ የቀረበው ይህ የሕግ ረቂቅ፤ በኢትዮጵያ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ከበሬታ መረጋገጥ እና ብሎም ሁሉን አቀፍ አስተዳደር መፈጠር የታለመ መሆኑን ይዘረዝራል።

ኮንግሬስማን ማይክል ሃዋርድ ኮፍማን በUS የተወካዮች ምክር ቤት የኮሎራዶ ክፍለ ግዛት ስድስተኛው የምክር ቤታዊ የአስተዳደር ክልል ተወካይ ናቸው።

ረቂቅ ሕጉ ያለበትን ሁኔታ እንዲያስረዱ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ፤ ከምክር ቤቱ አመራር አባላት ጋር ባደረግናቸው ንግግሮች “በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብትና አስተዳደር ጉዳዮች ያሉትን አማራጮች ለማየት ከሚያስችለን ስምምነት ላይ ደርሰናል፤” ይላሉ።

“የኢትዮጵያ መንግስት እስረኞችን እየፈታ ነው፤ አንዳንድ መሻሻሎችንም እያደረገ ነው፤ እናም በረቂቅ ሕጉ ላይ ድምጽ ከመ’ሰጠቱና ከመጽደቁ አስቀድሞ ነገሮችን ወደሚፈለገው አቅጣጫ ይወስዳል፤” የሚል አስተያየትም ተነስቷል። በእርግጥ እኔ በዚያ ግምት አልስማም። ለሁሉም የምናየው ይሆናል። ካልሆነም ረቂቅ ሕጉ እውን ወደሚሆንበት መንገድ እናመራለን።” የሚሉት ኮንግሬስማን ኮፍማን የጊዜ ገደቡ እየተጤነ መሆኑንም ጨምረው ገልጠዋል።

ሁኔታዎች ተሥፋ እንደተጣለባቸው ባይይዙና ቀደም ብለው እንደገለጹት የሕግ ረቂቁን ተፈጻሚ ወደሚያደርገው አማራጭ የሚኬድ ቢሆን፤ በእርግጥ ሕጉ ምን ዓይነት ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት ያስገኝ ይሆን? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄም ኮፍማን እንዲህ ይመልሳሉ።

“ዩናይትድ ስቴትስ በክልሉ ላላት በብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ለሚያደርገው ግንኙነቷ ቅድሚያ በመስጠት በኢትዮጵያ መንግስት የሚፈጽሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ለረዥም ጊዜ አይታ እንዳላየች ስታደርግ ቆይታለች። ያ! ፍጹም የተሳሳተ ነገር ነው። በመሆኑም ይሄ ያን ስህተት የማመን የመጀመሪያ እርምጃ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት በገዛ ዜጎቹ ላይ የሚፈጽመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም።”

የመቶ ሚልዮን ሕዝብ መኖሪያ የሆነችው፤ በአፍሪቃ ቀንድ ዋነኛዋ የዩናይትድ ስቴትስ ሃጋር የሆነችው ኢትዮጵያ፥ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ መሆኗ እየተዘገበ ነው። ለመሆኑ ያች ሃገር ቀውሱ ተባብሶ የከፉ ሁኔታዎች ውስጥ እንዳትወድቅ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ሊወስዳቸው የሚችላቸው እርምጃዎች ይኖሩ ይሆን? ለሚለውም ኮፍማን ጥረታቸው ያ እንዳይሆን መሆኑን ያስረዳሉ።

“ቀውስ በተንሰራፋበት የሚሆነውን እናውቃለን። እርግጥ ነው፤ የኢትዮጵያ መንግስት የገዛ ዜጎቹ ላይ ሽብር እየፈጸመ ነው። መንግስት አልባነት በኢራቅ ይሁን በሊቢያ ያደረገው ቢኖር፤ የአሸባሪዎች መፈልፈያ መሆን ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ሁኔታዎቹን መለወጥ አለበት። የዚህ ረቂቅ ሕግ መመሪያም ሆነ ሌላው እየሠራን ያለነው ያን ለመከላከል ነው።” ይላሉ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG