በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"እንደምን ከዚህ ደረስን?" .. ሁከት፡ ፈተናና ዘላቂ የሰላም መንገዶች


አቶ ይልማ አዳሙ፡ አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ እና አቶ ደረጀ ደምሴ ቡልቶ።
አቶ ይልማ አዳሙ፡ አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ እና አቶ ደረጀ ደምሴ ቡልቶ።

“… እርግጥ ያንን ሕግ ሲያወጡ 'በዚህ መልክ ነው አብሮ መኖር የሚያስችለን' ብለው ሊሆን ይችላል። ነገር ግን አንድን አገር እንደ እንዳትኖር ለማድረግ ከፈለግክ የምታመጣው የሕገ መንግስት መመዋቅር ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ዓይነት ነው።...” አቶ ደረጀ ደምሴ ቡልቶ።

“…ብልህ ቤተሰብ፥ ብልህ መሪ ያለው አገር ከዚህ አሰቃቂ ሁኔታ .. ከዚህ ጥፋት ምንድነው የተማርኩት ብሎ ይጠይቃል።…”አቶ ይልማ አዳሙ።

“…የኢትዮጵያ ህግ ሁሉም ሰው በህግ ዓይን እኩል ነው ይላል። 'ጠንካራ መንግስት' እፈልጋለሁ ስል ይሄን የማድረግ ችሎታ ያለው ማለት ነው።…” አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ።

ከፍተኛ ጉዳት ያስከተለ ብርቱ ሃዘን በአንድ ወገን፤ የዛሬና የነገ ፈተናዎች እንዲሁም ዘላቂ መፍትሔ ፍለጋው በሌላው የሚፈተሹበት ውይይት ነው።

በኢትዮጵያ በቅርቡ የደረሰውና በርካቶች በግፍ የተገደሉበት ጥቃት ካሳደረው ሃዘን እና የልብ ስብራት፤ ብሎም ከቀሰቀሰው የቁጣ ስሜት ባሻገር የዛሬውን ጉዳትና “እንዴት?” የሚለውን በአስተዋይ ልቦና መመርመር ብቻ ሳይሆን የነገውን የሩቅ መንገድ በአርቆ አሳቢነት ለመመዘን እና ሁነኛ መፍትሔዎችን ለመሻት ጭምር የሚጥር ዝግጅት ነው። የሃገርን እና የህዝብን መጭ ዕጣም ይዳስሳል።

አዎን! የችግሮቹን መንሴዎችም ሆነ ፈውሱን በቀጥታ ለማየት ጥረት መደረግ ያለበት ሰዓት አሁን ይመስላል::

ተወያዮቹ አቶ ይልማ አዳሙ፡ አቶ ደረጀ ደምሴ ቡልቶ እና አቶ ሙልጌታ አረጋዊ በየተሰማሩባቸው የሞያ መስኮች ከፍተኛ ዕውቀትና ልምድ ያካበቱና የተለያዩ የባሕል መሰረቶች ያሏቸው ናቸው። በውይይቱ ጠባይ ሳቢያ የማንነታቸውን ገጾች ከወትሮው ዘለግ ብለው ያስተዋውቁናል።

የውይይቱን ተከታታይ ክፍሎች ከዚህ ያድምጡ።

እንደምን ከዚህ ደረስን? - ክፍል አንድ
please wait

No media source currently available

0:00 0:31:08 0:00
እንደምን ከዚህ ደረስን? - ክፍል ሁለት
please wait

No media source currently available

0:00 0:20:19 0:00
እንደምን ከዚህ ደረስን? - ክፍል ሦስት
please wait

No media source currently available

0:00 0:28:22 0:00
እንደምን ከዚህ ደረስን? - ክፍል አራት
please wait

No media source currently available

0:00 0:22:15 0:00


XS
SM
MD
LG