በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የየመን ሁቲ አማፅያን በሳውዲ ዓረብያ ጥቃት ማድረሳቸው ተጠቆመ


የየመን ሁቲ አማፅያን በደቡብ ሳውዲ ዓረብያ ናጅራን ከተማ የጦር መሳሪያ መጋዘን ላይ ጥቃት አድርሰናል ሲሉ ዛሬ አስታወቁ።

የየመኖቹን ሁቲ ሸማቂዎች የሚወጋው ሳውዲ መራሹ ህብረት ቃል አቀባይ ሲናገር ጥቃቱ የተፈፀመው ፈንጂ በጫኑ፣ ያለነጂ የሚበርሩ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) መሆኑንና ሲቪሎች የሚጠቀሙበት ስፍራ ዒላማ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል። በጥቃቱ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ይኖር እንደሆን ግን ቃል አቀባዩ አልገለጹም።

ትናንት ሳውዲ ዓረብያ ከወደ የመን የተተኮሱ ሁለት የሁቲዎች ሚሳይሎችን አንደኛው “ወደ ታይፋና ወደ ጄዳ በማምራት ላይ እንዳሉ መትተናቸዋል” ስትል አስታውቃለች።

ሁቲዎቹ ሚሳይል “አልተኮስንም” ብለው አስተባብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG