በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሁቲ አማፂያን መሪ አሜሪካን አስጠነቀቁ


የመን
የመን

አሜሪካ በየመን የሚገኙትን የሁቲ አማጺያን ኢላማ የምታደርግ ከሆነ፣ የጦር መርከቦቿ ላይ ጥቃት እንደሚሰነዝሩ የቡድኑ መሪ ትናንት ረቡዕ አስጠንቅቀዋል።

ቀይ ባሕር ላይ በሚተላለፉ የንግድ መርከቦች ላይ እየጨመረ የመጣውን የሁቲ አማፂያን ጥቃት ለመግታት፣ አሜሪካ በዚህ ሳምንት አንድ ዓለም አቀፍ ጥምር ጦር አቋቁማለች፡፡

አገራቸውን ኢላማ የሚያደርግ ወይም ጦርነት የሚያውጅ ማንኛውንም አሜሪካዊ፣ እጃቸውን አጣጥፈው እንደማይመለከቱ የአማፂያኑ መሪ አብደል ማሌክ አል ሁቲ አስጠንቅቀዋል።

የአሜሪካ የጦር መርከቦችንም ሆነ ሌሎች ተጓዥ መርከቦችን፤ በሚሳዬል፣ ድሮን እና ሌላም ወታደራዊ መንገድ እንደሚያጠቁ አል ሁቲ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል፡፡

በእስራኤል እና ሐማስ መካከል ጦርነት መፈንዳቱን ተከትሎ፣ የሁቲ አማፂያን በቀይ ባሕር ላይ የሚተላለፉ እና በተለይም ከእስራኤል ጋር ግንኙነት ያላቸውን መርከቦች ሲያጠቁ ሰንብተዋል።

ይህ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ለምታካሂደው ጥቃት መልስ እንደሆነ በኢራን ይደገፋል የሚባለው አማፂው ቡድን አስታውቋል።

በአሜሪካ የሚመራ እና ሌሎች 10 የኔቶ አባል አገራትን ያካተተ ቡድን ቀይ ባሕር ላይ ቅኝት ለማድረግ በዝግጅት ላይ ነው።

የሁቲ አማፂያን ጥቃት፣ የመርከብ ኩባንያዎች ወደ አውሮፓ የሚያደርጉትን ጉዞ፣ በአፍሪካ ደቡባዊ አቅጣጫ በኩል ዞረው ረጅም ርቀት እንዲሄዱ አስገድዷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG