በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሁቲ ቁስለኛ ተዋጊዎች ከየመን እንዲወጡ እየተደረገ ነው


በየመን ሽምቅ ተዋጊዎች ይዞታ ሥር ባለችው ሳንዓ የሚገኙ የሁቲ ቁስለኛ ተዋጊዎች፣ ስዊድን ሊካሄድ የታቀደው የሰላም ድርድር ከመጀመሩ አስቀድሞ እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑ ታወቀ።

በየመን ሽምቅ ተዋጊዎች ይዞታ ሥር ባለችው ሳንዓ የሚገኙ የሁቲ ቁስለኛ ተዋጊዎች፣ ስዊድን ሊካሄድ የታቀደው የሰላም ድርድ ከመጀመሩ አስቀድሞ እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑ ታወቀ።

ቁስለኞቹ በአምቡላንስ እየተጫኑ በተመድ ቻርተርድ አውሮፕላን ለመጓዝ ወደ አየር ማረፊያ ነው እየተወሰዱ ያሉት። ሳዑዲ መራሹ ጣምራ ኃይልም፣ የቁስለኞቹን መውጣት እንዳጸደቀ ገልጧል።

የየመኑ ውጊያ አገሪቱን ረሀብ አፋፍ ላይ እንዳደረሳት ይታወቃል። ወደ 70% የሚሆነው የሀገሪቱ ምግብና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች የሚላኩት በወደብ በኩል መሆኑ ይታወቃል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG