በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግብፅ ከስወዝ ካናል የምታገኘው ገቢ እንደቀነሰ አስታወቀች


ፎቶ ፋይል፦ ካይሮ፣ ግብፅ
ፎቶ ፋይል፦ ካይሮ፣ ግብፅ

በድጋሚ የታደሰ

በየመን የሚገኙ የሁቲ አማጽያን በቀይ ባሕር ላይ በሚመላለሱ መርከቦች ላይ ጥቃት መፈጸም ከጀመሩ ወዲህ፣ ግብፅ ከስወዝ ካናል መተላለፊያ የምታገኘው ገቢ ከ40 እስከ 50በመቶ እንደቀነሰ የአገሪቱ ፕሬዝደንት አብደል ፋታህ ኤል ሲሲ ዛሬ ሰኞ አስታውቀዋል።

በከፍተኛ የገንዘብ ቀውስ ውስጥ ላለችው ግብፅ፣ ከስወዝ ካናል መተላለፊያ የምታገኘው ዋና የውጪ ገቢ ምንጯ ነው።

ከፍልስጤማውያን ጋር ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት በሚል የሁቲ አማጺያን ካለፈው ህዳር ወር ጀምሮ በቀይ ባሕር እና በኤደን ባሕረ ሰላጤ በኩል በሚያልፉና ከእስራኤል ጋር ግኑኝነት አላቸው በሚሏቸውን መርከቦች ማጥቃት ጀምረዋል።

ጥቃቱ የመርከብ ባለቤቶችን በቀይ ባሕር በኩል ሥምሪት እንዲያቆሙ እና አንዳንዶቹን ደግሞ በደቡባዊ አፍሪካ በኩል በሺሕ ኪሎ ሜትሮች ተጨማሪ ጉዞ እንዲያደርጒ አስገድዷል።

ግብፅ ከስወዝ ካናል በዓመት 10 ቢሊዮን ዶላር ታገኝ እንደነበር ኤል ሲሲ ማስታወቃቸውን የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

ቀይ ባሕርን ከሜዲትሬንያን ባሕር በሚያገናኘው ሱወዝ ካናል በኩል የሚተላለፈው የመርከቦች ትራፊክ በ42 በመቶ መቀነሱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለፈው ወር አስታውቆ ነበር። ሸቀጥ የሚያስተላልፉ መርከቦች ቁጥር ደግሞ 67በመቶ ቅናሽ ማሳየቱም ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG