በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እማኝነት በኮንግረስ - “ኤርትራ፡- ችላ የተባለች አካባቢያዊ ሥጋት”

የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ሕንፃ
የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ሕንፃ

“ኤርትራ እራሷን እንደ ዳዊት ዩናይትድ ስቴትስን እንደ ጎልያድ ማየት ከፈለገች የሚደርሱባት ቁስለቶች ሁሉ በራሷ የሚደርሱባት፣ የምትወነጭፋቸው ጠጠሮችም የሚወርዱት በራሷ ሕዝብ ላይ ነው” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ አስታውቀዋል፡፡

እማኝነት በኮንግረስ - “ኤርትራ፡- ችላ የተባለች አካባቢያዊ ሥጋት”
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:00 0:00

“ኤርትራ እራሷን እንደ ዳዊት ዩናይትድ ስቴትስን እንደ ጎልያድ ማየት ከፈለገች የሚደርሱባት ቁስለቶች ሁሉ በራሷ የሚደርሱባት፣ የምትወነጭፋቸው ጠጠሮችም የሚወርዱት በራሷ ሕዝብ ላይ ነው” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ አስታውቀዋል፡፡

ረዳት ሚኒስትሯ ትናንት በዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው በሰጡት ማብራሪያ አሁን በኤርትራና በአሜሪካ መካከል ያለው ግንኙነት ዋሺንግተን እንዲኖር የምትፈልገው ዓይነት አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

“ኤርትራ፡- ችላ የተባለች አካባቢያዊ ሥጋት” በሚል ርዕስ በተካሄደው በዚህ የእማኝነት መድረክ ላይ ቀርበው የተናገሩ ሌሎችም ምሥክሮች የኤርትራ መንግሥት እየተከተለ ነው በሚሉት አቅጣጫና የየራሣቸውን የመፍትሔ ሃሣቦች አቅርበዋል፡፡

የኤርትራን መንግሥት ምላሽ ለማግኘት ዋሺንግተን ዲሲ ወደሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ፣ ኒው ዮርክ ወደሚገኘው የኤርትራ ሚሲዮን፣ ወደ አሥመራም ደውለን ያደረግናቸው ሙከራዎች ለጊዜው አልተሣኩም

በሌላ በኩል ግን የኤርትራ-አሜሪካዊያን ድርጅት የሚባል ቡድን ባወጣው መግለጫ ላይ በኤርትራ ላይ የተካሄደውን የትናንቱን አማኝነት “ቅንነት ከጎደለው መረጃ የተነሣ” ሲል ሰይሞታል፡፡

ዝርዝሩን የያዘውን ሪፖርት ከላይ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በኤርትራ ላይ የተካሄደውን እማኝነት ሙሉ በሙሉ ለማየት ከታች ያለውን ማገናኛ ተጭነው ይከተሉ፡፡

https://www.youtube.com/watch?time_continue=4202&v=ciVeLgOCHzI

XS
SM
MD
LG