በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“በሆቴል ሩዋንዳ” ሰብአዊነታቸው የተተረከላቸው ሩሴስባጊና ፍርድ ቤት ቀረቡ


በሆቴል ሩዋንዳ ፊልም ሰብአዊ ጀግንነታቸው የተተረከላቸው ፖል ሩሴስባጊና ሀምራዊ ዩኒፎርም ለብሰው የሚታዩት ሲሆኑ ምስሉ የተወሰደእው መስከረም 25/2020 ዓም ነው፡፡
በሆቴል ሩዋንዳ ፊልም ሰብአዊ ጀግንነታቸው የተተረከላቸው ፖል ሩሴስባጊና ሀምራዊ ዩኒፎርም ለብሰው የሚታዩት ሲሆኑ ምስሉ የተወሰደእው መስከረም 25/2020 ዓም ነው፡፡

ሆቴል ሩዋንዳ በተባለውና ለኦሳክር ሽማልት በታጨው ፊልም የሰብአዊ አገልግሎት ታሪካቸው የተወሳላቸው ፖል ሩሴስባጊና፣ አማጽያንን በመደገፍ ተከሰው ከትናንት በስቲያ ረቡዕ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡

ቤተሰቦቻቸውና የሰብአዊ መብት ተሟጎች ግን ግለሰቡ በሩዋንዳ መንግሥት የታገቱ መሆናቸውን በመግለጽ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጠይቀዋል፡፡

ፖል ሩሴስባጊና ባለፈው ረቡዕ ከሩዋንዳ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው ፍርድቤት፣ በዳኛ ፊት ከቀረቡት 20 ተከሳሾች መካከል አንዱ ናቸው፡፡

እኤአ በ1994 በሩዋንዳ በተካሄደው የዘር ፍጅት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት በማትረፍ ጀግንነት የተወደሱት ግለሰብ፣ ዛሬ የሩዋንዳ መንግስትን የሚቃወሙ አማጽያንን ይደግፋሉ በሚል በሽብርተኝነት ተከሰዋል፡፡

ቤተሰቦቻቸውና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ደግሞ ከዱባይ ኤፖርት ይጓጓዙበት ከነበረው የግል አውሮፕላን ያለፈቃዳቸው ታፍነው ወደ ሩዋንዳ ዋና ከተማ እንዲመጡ የተገደዱ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

የሩሴስባጊና ጠበቃ ጋቴራ ጋሻባና እንዲህ ይላሉ ፦

“ሩሴስባጊና ወደ ሩዋንዳ የመጡት በህገወጥ መንገድ መሆኑን መግለጽ እፈልጋለሁ፣ ከሚኖሩበት አገር ተላልፈው ስለተሰጡ አይደለም የመጡት፣ በራሳቸው በጎ ፈቃድ እንኳ ፈልገው አልመጡም፣ ከፍላጎታቸው ውጭ ራሳቸውን ያገኙት ሩዋንዳ ውስጥ ነው”

ኪምሁሩራ በሚገኘው የሩዋንዳ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዳያቸው በታየበት ወቅት፣ ሩሴስባጊና ፍርድቤቱ ጉዳያቸውን የማየት ሥልጣን የሌለው መሆኑን ተከራክረዋል፡፡ ምክንያቱም እሳቸው ያለፈቃዳቸው ታፍነው የመጡ የቤልጅዬም ዜጋ ናቸው፡፡

የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ በበኩላቸው፣ ሩሴስባጊና የተያዙበትን መንገድ አግባብነት

“በሆቴል ሩዋንዳ” ሰብአዊነታቸው የተተረከላቸው ሩሴስባጊና ፍርድ ቤት ቀረቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:26 0:00



በመግለጽ እንደሚከተለው አስተባብለዋል፡፡

“የተደረገ ጠለፋ የለም፡፡ እሳቸውን እዚህ በማድረስ ሂደት ላይ የተሰራ ጥፋት የለም፡፡ እሳቸው ወደዚህ የመጡት ራሳቸው ባመኑበትና በፈለጉበት መንገድ ነው፡፡”

የክሱ ሂደት በመላው ዓለም ቁጣን ቀስቅሷል፡፡ 37 የሚደርሱ የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት፣ ለፕሬዚዳንት ካጋሜ ፈርመው በላኩት ደብዳቤ፣ ሩሴስባጊና ከካንሰር ህመም ያገገሙ በመሆናቸው፣ ለሰአብዊነት ሲባል በአስቸኳይ እንዲለቋቸው ጠይቀዋል፡፡ ወደ ሩዋንዳ የተወሰዱበት ህገወጥ መንገድም እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ሁኔታውን እየተከታተለ መሆኑን ገልጾ፣ ከፍተኛ የሥልጣን እርከን ደረጃ ካላቸው የሩዋንዳ መንግሥት ባለልሥጣናት ጋር እየተነጋገረበት መሆኑን አስታውቋል፡፡ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ነድ ፕራይስ ይህን ብለዋል

“ሚስተር ሩሴስባጊና በተከሰሱበት ጉዳይ የሚከናወነው የፍርድ ሂደት፣ ግልጽና ፍትሃዊ መሆኑን፣ የህግ የበላይነት የተከበረበትና፣ ሩዋንዳ የገባችውን ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብት ግዴታዎች ጋር የሚስማማ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተን መከታተላችንን እንቀጥላለን፡፡”

ሁለቱ የሩሴስባጊና ሴት ልጆች፣ የጠበቆች ቡድንና ደጋፊዎች የፍርዱን ሂደት በድረ ገጽ የተከታተሉ ሲሆን፣ ስለ ሂደቱም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በሩሴስባጊና ፋውንዴሽን ውስጥ የሚሰሩት ብሬን ኢንድለስ ችሎቱ “ለይስሙላና ታይታ የሚካሄድ ችሎት ነው” በማለት ገልጸውታል፡፡ አብረው ስለቀረቡ ሌሎች ተከሳሶሽም ጭምር ሲናገሩ ይህን ብለዋል

“እነዚህ ተከሳሾች እኮ ህይወታቸውና ምናልባትም እድሜ ይፍታህ የሚፈረድባቸው ናቸው፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ከጎናቸው ቆሞ መከላከያቸውን የሚያግዛቸው ጠበቃ የላቸውም፡፡ ጠበቆቹ ችሎቱ ከሚካሄድበት ክፍል በስተጀርባ እንዲሆኑ ተደርገዋል፡፡ ያ መሆኑን ማየት ብቻ በራሱ አስደናቂ ነገር ማየት ነው፡፡

ከአገር ውጭ የሚኖሩት የሩሴስባጊና ሴት ልጅ በእስር ቤት የአባታቸው ጠባቂ መሆኑን ከሚገልጽ አንድ ሰው፣ ተደጋጋሚ የማስፈራሪያ ስልኮችና የቴክስት መልዕክቶች እንደሚደርሳቸው ተናግረዋል፡፡

ሰውየው "አባትሽን ከእስር ቤት እንዲያመልጥ ልረዳው እችላለሁ" በማለት ለማግባባት እንደሚሞክርና ይህም የማመልጥ ሙከራ እንዳደረገ በማሰብ ለሞት የሚያበቃውን ክስ አባቴ ላይ ለመመስረት የተሰናዳ ወጥመድ ነው ብለዋል፡፡ የሩሴስባጊና ሴት ልጅ ኬሪን ካኒምባ አክለውም ይህን ብለዋል

“ይህን ዘዴ እንደሚጠቀሙ ያወቅነው አሁን ነው፡፡ ይህ ለአባታችን ካለን ሀዘንና ቤተሰባችን አሁን ካለበት ሁኔታ አንጻር ከሰብአዊነት ውጭ የሆነ ነገር ነው፡፡ ይህንን ዘዴ ሳይሆን ህጋዊውን መንገድ ተጠቅመን አባታችንን ከእስር ቤት እናወጣዋለን፡፡”

ሩሴስባጊና በተመሰረተባቸው ክስ ጥፋተኝነቱን አልተቀበሉም፡፡ ዳኛውም፣ ፍርድቤቱ ጉዳዩን የማስቻል ሥልጣን ያለው መሆን አለመሆኑን ለመወሰን እኤአ ለየካቲት 26 ቀጠሮ መስጠታቸው ታውቋል፡፡

(የቪኦኤ ዘጋቢ ሳሌም ሶሎሞን ካሰናዳችው ዘገባ የተወሰደ፡፡)

XS
SM
MD
LG