የሆቴል ዘርፉ፣ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ችግሮች እየተፈተነ እንደኾነ የገለጸው የኢትዮጵያ የሆቴል እና ቱሪዝም አሠሪዎች ፌዴሬሽን፣ መንግሥት የሆቴሎችን የዕዳ መክፈያ ጊዜ ወደ 30 ዓመት እንዲያራዝም ጠየቀ፡፡
የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ዶር. ፍትሕ ወልደ ሰንበት ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ የባንክ ዕዳ መክፈያ ጊዜው በማጠሩ ምክንያት፣ ብዙ ሆቴሎች በዐቅም ማነስ ከገበያው እየወጡ እንደኾኑ ጠቅሰው፣ መንግሥት፣ ዘርፉን በልዩ ኹኔታ እንዲመለከተው ጠይቀዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ፣ ይመለከታቸዋል ያልናቸውን የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች አስተያየት እና ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለዛሬ አልተሳካም፡፡
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም