በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ በታጣቂዎች ጥቃት 13 ሰዎች እንደተገደሉ ተገለጸ


በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ በታጣቂዎች ጥቃት 13 ሰዎች እንደተገደሉ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:02 0:00

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ በታጣቂዎች ጥቃት 13 ሰዎች እንደተገደሉ ተገለጸ

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ በጆጅ ቀበሌ፣ ትላንት ማክሰኞ ታጣቂዎች አደረሱት በተባለ ጥቃት፣ ከደርዘን በላይ ሰዎች እንደተገደሉ፣ የቀበሌው አስተዳደር አስታወቀ።

የጆጅ ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ አባዋ ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ፣ ምርት ለመሰብሰብና የቀን ሥራ ለመሥራት ወደ ቡሬ ወረዳ ጫቦ ቀበሌ በመሔድ ላይ ነበሩ ያሏቸው፣ በቁጥር 13 የኾኑ ሰዎች፣ በፋኖ ታጣቂዎች እንደተገደሉ ገልጸዋል፡፡

ከዐይን እማኞች አንዱ እንደኾኑ በስልክ የነገሩን ግለሰብ ደግሞ፣ ከምሥራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ሀሮ ቀበሌ የመጡ ናቸው ያሏቸው ታጣቂዎች ጥቃቱን እንደፈጸሙ ተናግረዋል።

የፋኖ ታጣቂዎች በወረዳው እንደሚንቀሳቀሱ የጠቀሰው የኪረሙ ወረዳ አስተዳደር በበኩሉ፣ ወደ አሙሩ ወረዳ ጆጅ ቀበሌ ገብተው ጥቃት ስለመፈጸማቸው ግን አላረጋገጥኹም፤ ብሏል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ የአሜሪካ ድምፅ ያናገራቸውና ጥቃቱን ፈጽሟል የተባለው የቡሬ ወረዳ አካባቢ የፋኖ ታጣቂ የሻለቃ አደረጃጀት መሪ፣ ድርጊቱ በእነርሱ እንዳልተፈጸመ አስተባብለዋል፡፡ ጥቃቱን እንደሚያወግዙ አክለው የገለጹት የፋኖ አደረጃጀት መሪው፣ “የመከላከያ አባላትን ጨምሮ ማንኛውንም አካል በብሔር ለይተን ጥቃት አናድርስም፤” ብለዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG