ዋሺንግተን ዲሲ —
እ.ኤ.አ መስከረም 2016ዓ.ም. ቁጥራቸው ወደ 10ሽህ 6መቶ ሰዎች በቀይ ባህር እና በኤደን ባህረ ሰላጤ በኩል አድርገው የመን ደርሰዋል “ሪሊፍ ዌብ” የሚባለው የመረጃ ማዕከል ባወጣው ሪፖርት።
በሌላ ዘገባ በዚሁ ዓመት ሜዲቴራኒያን ባህርን ለማቋረጥ ሲሞክሩ ህይወታቸውን ያጡ ስደተኞችና ፍልሰተኞች ቁጥር ከምንጊዜውም መብለጡን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ገልጹዋል።
አብላጫውን ቁጥር የያዙት ኢትዮጵያውያንና ሶማሊያውያን መሆናቸው ተገልጿል፡፡ ስደተኞቹ የመን እንደደረሱ በሚሰጡት ቃል የታጠቁ አዘዋዋሪዎች ጠረፉ ላይ ተጠባብቀው አዲስ ገቢዎቹን ጠልፈው እንደሚወስዷቸው ብሎም ማስለቀቂያ ገንዘብ እንደሚጠይቁዋቸው፤ ይሄን ካለደረጉ ግን በደልና እንግልት እንደሚፈፅሙባቸዋል ተናግረዋል።
እስከ አሁንም ከሃምሳ የሚበልጡ አዋቂ ሴቶችና ልጃገረዶች የመን ጠረፍ እንደደረሱ ተጠልፈው መወሰዳቸውንና አሁን የት እንዳሉ እንደማይታወቅ የሪሊፍ ዌቡ ሪፖርት አመልክቷል።
ሊሳሽ ላይን ከጄኔቫ የላከችውን ዘገባ ቆንጂት ታዬ ታቀርባለች።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡