በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያና የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የጋራ መግለጫ


የኢትዮጵያና የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሞቋዲሹን ከጎብኙ በኋላ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።

የኢትዮጵያና የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሞቋዲሹን ከጎብኙ በኋላ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።

የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁና የኤርትራው አቻቸው ኦስማን ሳልሕ ከሶማልያ ህዝብና አመራሩ ጋር መቆሙን እንደሚቀጥሉ ደግመው አረጋግጠዋል።

የሶማልያ ፌደራል መንግሥት የሀገሪቱን የረዥም ጊዜ ማገገምን ለማጎላመት በሚያደርገው ጥረት መላ ዓለምቀፍ ማኅበረሰብ ተባብሮ ፌደራል መንግሥቱን እንዲደግፍም ጥሪ አቅርበዋል።

በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉት ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉ ለሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰሩ ሁለቱ ሚኒስትሮች ጥሪ አድርገዋል።

ለሉዓላዊነት፣ ለግዛታዊ ክብርና ለፖለቲካዊ ነፃነት ያላቸው የጋራ እውቅና እንደተጠበቀ ሆኖ የክልሉን ፀጥታ፣ ብልፅግናና መረጋጋት ያላቸውን ቁርጠኛነት ባለወጡት የጋራ መግለጫ አስምረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG