በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ቀንድ ከዚህ በፊት ከታየው የከፋ ቸነፈር ገጥሞታል


የአፍሪካ ቀንድ ከዚህ በፊት ከታየው የከፋ ቸነፈር ገጥሞታል
የአፍሪካ ቀንድ ከዚህ በፊት ከታየው የከፋ ቸነፈር ገጥሞታል

በአፍሪካ ቀንድ በአሁኑ ወቅት የሚታየው የድርቅ ሁኔታ ሩብ ሚሊዮን ሰዎችን ከገደለውና ከ 12 ዓመታት በፊት በእአአ 2011 ከታየው የባሰ እንደሆነ የቀጠናው የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) የአየር ትንበያ ማዕከል ዛሬ አስጥንቅቋል፡፡

ማዕከሉ በተጨማሪም በመጪው ሦስት ወራት ከተለመደው በታች የዝናብ መጠን እንደሚጠበቅ አስታውቋል፡፡ ይህም በሶማሊያ፣ በኢትዮጵያና ኬንያ ለስድስተኛ ተከታታይ ወቅት ዝናብ ሳይጥል እንደሚቀር አመላካች ነው ብሏል ማዕከሉ።

በሶማሊያ ለሦስት ዓመታት የቆየው ድርቅ በአሥር ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ሲገድል፣ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ደግሞ መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያስታውቃል።

በሶማሊያ የተከሰተው ሞት ከ12 ዓመታት በፊት ከነበረው በእርግጠኝነት በሚባል ደረጃ እንደሚልቅ በአገሪቱ የተመድ አስተባባሪ አስጠንቅቀዋል።

በሶማሊያ፣ በኢትዮጵያና ኬንያ በድምሩ 23 ሚሊዮን ሰዎች ከፍተኛ የምግብ ዋስትና እጦት የተጋረጠባቸው መሆኑን የተመድ የምግብ ፕሮግራም (ፋኦ) አስታውቋል፡፡ 11 ሚሊዮን የሚሆኑ የቤት እንስሳት አልቀዋል፡፡

በዩክሬን እየተካሄደ ያለው ጦርነት በተለምዶ አፍሪካን ይረዱ የነበሩ የአውሮፓ ለጋሾች ትኩረታቸው እዛው እንዲቀር አድርጓል።

የኢጋድ ሊቀመንበር ወርቅነህ ገበየሁ መንግሥታትና አጋሮች በጣም ከመዘግየቱ በፊት መላ እንዲዘይዱ ጥሪ አድርገዋል።

XS
SM
MD
LG