በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እሬቻ አዲስ አበባ ላይ ተከበረ


ሆራ ፊንፊኔ እሬቻ - 2014
ሆራ ፊንፊኔ እሬቻ - 2014

የሆራ ፊንፊኔ የእሬቻ በዓል ዛሬ ቁጥሩ እጅግ የበዛ ታዳሚ በተገኘበት አዲስ አበባ ላይ ተከብሯል።

በበዓሉ ላይ ከሁሉም የኦሮምያ ክልል ዞኖችና ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች፣ እንዲሁም ከጎረቤት ሃገሮችና ዓለማቀፉን ማኅበረሰ የወከሉ ታዳሚዎች መገኘታቸውና የደመቀ እንደነበርም ታውቋል።

በበዓሉ ላይ ገዥውን የብልፅግና ፓርቲንና መንግሥትን የሚያወግዙ መፈክሮችን ያሰሙ ተሳታፊዎችም ታይተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ የዘንድሮው ሆራ ፊንፊኔ እሬቻ በዓል ሀገሪቱ የተለያዩ ችግሮች በተጋረጡባት ሁኔታ ውስጥም ቢሆን በሰላም መከበሩን ተናግረዋል። ከንቲባዋ አክለውም በበዓሉ መዳረሻም በነበረው የእሬቻ ሳምንት ከተማዪቱ ውስጥ የተለያዩ ዝግጅቶች መከናወናቸውን አስታውሰዋል።

የተቃውሞ ድምፅ ያሰሙትን በሚመለከትም ወ/ሮ አዳነች ሲናገሩ “የህወሓት አጋር የሆነው ሸኔ የላካቸው ሰዎች በዓሉን ሊረብሹ ሞክረዋል፤ የእሬቻ ወግና ሥርዓት ግን ይሄንን የሚፈቅድ አይደለም” ብለዋል።

ከንቲባዋ “ሸኔ” ሲሉ የገለፁት ራሱን “የኦሮሞ ነፃነት ጦር” ብሎ የሚጠራው ቡድን እስካሁን በጉዳዩ ላይ ያለው የለም።

የአሜረካ ድምፅ የዘንድሮውን የእሬቻ በዓል ከሥፍራው በስፋት ለመዘገብ ያደረገው ተደጋጋሚ ጥረት ከአዘጋጆቹ የይለፍ ፈቃድ ባለመገኘቱ አልተሳካም።

እሬቻ አዲስ አበባ ላይ ተከበረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:45 0:00


XS
SM
MD
LG