በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ካሪ ላም ሥልጣናቸውን እንዲለቁ ተጠየቀ


የቤጂንግ ወገንተኛዋ የሆንግ ኮንግ አስተዳዳሪ ካሪ ላም ሥልጣናቸውን እንዲለቅቁ የአፍቃሪ ዲሞክራሲ ትግል አቀንቃኙ ጃሹዋ ዎንግ እየጠየቁ ናቸው።

ዛሬ ከእስር ቤት የተለቀቁት ጃሹዋ ዎንግ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ወደቤጅንግ አሳልፎ መስጠትን የሚመለከተውን አዋጅ በመቃወም የቀጠለውን ግዙፍ ህዝባዊ እንቅስቃሴ እቀላቀላለሁ ብለዋል።

እኤአ በ2014 የተካሄደውና "ባለዣንጥላው አመፅ" የሚል ቅፅል ስም የተሰጠው የተቃውሞ እንቅስቃሴ መሪዎች አንዱ የነበሩት ዎንግ ከአመፅ በተያያዘ ለሁለት ወር ታስረው ተለቀዋል።

ካሪ ላም ሥልጣናቸውን መልቀቅ አለባቸው ያሉት ጃሹዋ ዎንግ አስተዳዳሪዋ የማይለቁ ከሆነ መሰረታዊ ሰብዓዊ መብቶች እና ነፃነታችንን እስክናገኝ እንቀጥላለን ብለዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ጃፓን ውስጥ በሚከፈተው የ ጂ 20 የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለሚያገኙዋቸው ለቻይናው አቻቸው ሺ ዢን ፒንግ የሆንግ ኮንግን ጉዳይ እንደሚያነሱባቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዎ አስታውቀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG