በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሆንግ ኮንግ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ


በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የዲሞክራሲ ደጋፊዎች ትላንት በሆንግ ኮንግ መንገዶች ላይ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል። በሳምንት ማብቂያዎች ላይ የሚካሄዱት ፀረ መንግሥት ስልፎች 11ኛ ሳምንታቸውን ይዘዋል።

የሲቪል ሰብአዊ መብት ግንባር የተባለው በሆንግ ኮንግ የሚካሄደውን ተቃውሞ የሚያስተባብረው ቡድን ትላንት ብሄራዊ ግጭት አልባ ሰልፍ እንዲካሄድ ጥሪ አድርጎ ነበር።

ከዚህ ቀደም የተቃውሞ ሰልፈኞቹ ከፖሊሶች ጋር ሲጋጩ እንደነበር የሚታውቅ ነው። በሆንግ ኮንግ ዓለም ቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ ላይ ባለፈው ሳምንት ለሁለት ቀናት በተካሄደው የተቃውሞ ስለፍ ግጭት ታክሎበት ወደ 1,000 የሚጠጉ የአውሮፕላን በረራዎች ተሰርዘው ነበር።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG