በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና የሆንግ ኮንግ የተቃውሞ ሰልፈኞችን አስጠነቀቀች


ሆንግ ኮንግ ውስጥ ከሁለት ወራት በላይ ለሆነ ጊዜ ሲካሄድ የቆየው ከባድ ተቃውሞ ከተማዋን ማሽመደመዱን መስረት በማድረግ፣ ቻይና ለተቃውሞ ሰልፈኞቹ ከባድ ማስጠንቀቅያ ሰጥታለች።

የቻይና መንግሥት የሆንግ ኮንግና የማካኦ ጉዳይ ጽህፈት ቤት ቃል አቀባይ ያንግ ጓንግ ዛሬ ቤዢንግ ውስጥ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የከባድ ተቃውሞ ሰልፎቹ መሪዎች ከቅጣት እርምጃ እንዳማያመልጡ ተናግረዋል።

ለሳምንታት ያህል ሲካሄዱ የቆዩት ከባድ የተቃውሞ ስልፎች የገንዘባዊ ተቋማት ማዕከል በሆነችው ሆንግ ኮንግ የከፋ ፖለቲካዊ ቀውስ አስከትለዋል። እአአ በ1997 ብሪታንያ ለቻይና ካስረከብቻት ወዲህ ሆንግ ኮንግ ይህን ያክል የከፋ ቀውስ ገጥሟት እንደማያውቅ ተዘግቧል።

ተከሳሾች ለፍርድ ሂደት ወደ ቻይና እንዲላኩ የሚፈቅድ የህግ ረቂቅን በመቃወም ነበር የተቃውሚው እንቅስቃስሴ ባለፈው ሰኔ ወር የጀመረው። አሁን የህጉ ረቂቅ የተሰረዘ ቢሆንም የተቃውሞው እንቅስቃሴ ሰፍቶ የተሻለ ዴሞክራሲ ወደ መጠየቅ አምርቷል።

ቃል አቀባይ ያንግ ጓንግ የጥቂት ወንጀለኞች ቡድን ሆንግ ኮንግን ወደ “አደገኛ ጉድጓድ” ገፍተሯል ካሉ በኋላ ትዕግስታችንን በድክመት ባይገምቱት ይሻላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። “በእሳት የሚጫወቱት፣ በዛው ያልቃሉ” ሲሉም አክለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG