በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሆንግ ኮንግ የተቃውሞ እንቅስቃሴ


ሆንግ ኮንግ ውስጥ ለአራት ወራት ያህል ሲካሄድ የቆየው የተቃውሞ እንቅስቃሴ በከተማይቱ ምክር ቤት አዳራሽ ድረስ ደርሷል።

የከተማይቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኬሪ ላም ስለ ዓመታዊ ፖሊሲያቸው የሚገልፅ ፁሁፍ ለምክር ቤቱ ሲያነቡ የዲሞክራሲ ደጋፊዎች በከፍተኛ ድምፅ ተቃውሞ በማሰማታቸው ንግግራቸውን ለማቋረጥ ተገደዋል።

ተቃውሞው የጀመረው ላም ገና ወደ ምክር ቤቱ ሲገቡ ሲሆን የዲሞክራሲ ደጋፊ የምክር ቤት አባላት በደም የተነከሩ የመሪዋ እጆችን የሚያሳዩ ምልክትቶች ይዘው ታይታዋል።

የተቃዋሚዎቹ ጩኸት ላም ንግግር እስከጀመሩበት ጊዜ ድረስ በመቀጠሉ ለአጭር ጊዜ ከምክር ቤቱ ለመውጣት ተገደዋል። ወደ ምክር ቤቱ ተመልሰው ማንበቡን ለመቀጠል ቢሞክሩም ተቃውሞው በመቀጠሉ የምክር ቤቱ ካውንስል ፕሬዚዳንት አንድሪው ልዩንግ ስብሰባውን በተኑት።

ኬሪ ላም በመጨረሻ ንግግራቸውን በቴሌቪዥን አሰሙ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG