በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሕገ ወጥ መንገድ የገባ 1.7 ቢሊዮን ዶላር ሆንግ ኮንግ ላይ ተያዘ


በሆንግ ኮንግ ጉምሩክ በጉዳይ ዙሪያ መግለጫ በተሰጠ ወቅት ማስረጃዎች ቀርበዋል እአአ የካቲት 16/2024
በሆንግ ኮንግ ጉምሩክ በጉዳይ ዙሪያ መግለጫ በተሰጠ ወቅት ማስረጃዎች ቀርበዋል እአአ የካቲት 16/2024

የሆንግ ኮንግ ባለሥልጣናት፣ መነሻው ከሕንድ የሆነ እና በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ፣ ሕጋዊ ለማድረግ በሚደረግ ሂደት ውስጥ የነበረን 1.7 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር መያዛቸውን አስታውቀዋል።

እሰከ አሁን ድንበር ተሻጋሪ ከሆኑ እና በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ፣ ሕጋዊ ለማድረግ በሚደረጉ ወንጀሎች ከታዩት ትልቁ ነው ተብሏል።

ገንዘቡ እና ውድ ጌጦች በፕላስቲክ ከረጢቶች ታጭቀው መያዛቸውም ታውቋል።

አብዛኛው ገንዘብ የመጣው ከሕንድ እንደሆነ ባለሥልጣናት ተናግረዋል። ገንዘቡ፣ በሕንድ ከሚገኙና፣ በበይነ መረብ እያጭበረበርሩ ገንዘብ በመሰብሰባቸው በመንግስት ከታገዱ ሁለት ኩባያዎች ተልኮ ሆንግ ኮንግ እንደገባም ታውቋል።

ሰባት ግለሰቦች ተጠርጥረው እንደታያዙ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ሆንግ ኮንግ ላላ ያለ የዓለም አቀፍ ባንክ እና ንግድ ደንብ ስላላት፣ በቀላሉ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ከፍቶ መንቀሳቀስ በመቻሉ፣ ለሕገ ወጥ ገንዘብ አስተላላፊዎች ተመራጭ ሆናለች ተብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG