በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሆንግ ኮንግ ም/ቤት ፀረ መንግሥት ተቃውሞ የቀሰቀሰውን የህግ ረቂቅ ሰረዘ


የሆንግ ኮንግ ምክር ቤት በከተማይቱ ሲካሄድ የቆየውን ፀረ መንግሥት ተቃውሞ የቀሰቀሰውን የህግ ረቂቅ በኦፊሴል ሰርዟል። የህጉ ረቂቅ በወንጀል የሚጠረጠሩ ሰዎች ወደ ቻይና ተልከው እንዲዳኙ የሚያደርግ ነበር።

ለህጉ መርቀቅ መንስዔ የሆነው በግድያ የተጠረጠረው ሰው ከሆንግ ኮንግ እስር ቤት ተፈቷል። ለታይዋን ባለሥልጣኖች እጁን የመስጠት እቅድ እንዳለው ገልጿል።

ይሁንና የተቃውሞ ሰልፈኞቹና ምክር ቤት ውስጥ ያሉት ተቃዋሚዎች የተወሰደው ዕርምጃ በቂ አይደለም በማለት አምስቱን ነጥቦች ለመንግሥት ከማቅረብ ወደ ኋላ አንልም ብለዋል።

ነፍሰ ጡር ፍቅረኛውን በአስከፊ ሁኔታ በገደለው የ20 ዓመት ዕድሜ ቶንግ - ኬይ ምክንያት ነው ታቃውሞ ሲካሄድ የቆየው። ከፊል ራስ ገዝ የሆነችው የቻይና ከተማ ሆንግ ኮንግ በወንጀል የሚጠረጠሩትን ሰዎች ወደ ቻይና ለመላክ የሚያስችል የህግ ረቂቅ የነደፈችው ቻንን የመሳሰሉትን ተጠርጥሪዎች መሰረት በማድረግ ነበር።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG