በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጥገኝነት የጠየቁ የ500 ሶማሊያ ተወላጆች ጉዳይ ዛሬ ይወሰናል


የዩናይትድ ስቴትስ የሀገር ደኅንነት ሚኒስቴር ዩናይትድ ስቴትስ ጥገኝነት የጠየቁ አምስት መቶ የሶማሊያ ተወላጆች የተሰጣቸው ጊዜያዊ ከለላ ይራዘም እንደሆን ዛሬ ይወስናል።

የዩናይትድ ስቴትስ የሀገር ደኅንነት ሚኒስቴር ዩናይትድ ስቴትስ ጥገኝነት የጠየቁ አምስት መቶ የሶማሊያ ተወላጆች የተሰጣቸው ጊዜያዊ ከለላ ይራዘም እንደሆን ዛሬ ይወስናል።

ጉዳዩ ከሚመለክታቸው ጥገኝነት ፈላጊዎች ውስጥ አብዛኞቹ ያሉት ብዛት ያላቸው ሶማሊያ አፍሪካውያን በሚኖሩባት ሚኒሶታ ክፍለ ሃገር ነው።

ቁጥራቸው ከሃያ ሁለት የሚበልጥ የዩናይትድ ስቴትስ የመወሰኛ ምክር ቤት አባላት ለአገር ደኅንነት ሚስኒስትሩዋ ኪርስቲን ኔልሰን በላኩት ደብዳቤ የሃገራቸውን ብጥብጥ ሸሽተው ዩናይትድ ስቴትስ ለተጠለሉት ሶማሊዎች ጊዚያዊ ከለላው እንዲራዘምላቸው ተማፅነዋል።

የሚኔሶታዋ ሴኔተር ቲና ስሚዝ ለቪኦኤ የሶማሊኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል ሶማሊያ ውስጥ አሁንም አደጋ ስላለ እነዚህ ሰዎች አሁን ያላቸውን የኢሚግሬሽን ከለላ ቢነፈጉ ወደሃገራቸው እንዲመለሱ፣ ሌላ ሃገር ጥገኝነት እንዲፈልጉ ያደርጋል። ያ ደግሞ ቤተሰቦችን በመነጣጠል ሰብዓዊ ቀውስ ይፈጥራል ሲሉ አሳስበዋል።

ሶማሊያዎቹ አሁን ያላቸው ጊዜያዊ ጥበቃ ወይም ከለላ የሚያበቃው እኤአ መስከረም 17 ቀን መሆኑ ታውቁዋል። ልክ ከሁለት ወር በኋላ መሆኑ ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG