በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቤት ውስጥ ሕክምና አገልግሎት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዘመን​


የብርሃን የቤት ውስጥ ህክምና አገልግሎት ድርጅት ሊቀ መንበር እና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍስሃ ወልዴ ሞላልኝ።​
የብርሃን የቤት ውስጥ ህክምና አገልግሎት ድርጅት ሊቀ መንበር እና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍስሃ ወልዴ ሞላልኝ።​

“በየቀኑ እስከ አምስት መቶ የሚደርሱ ሕሙማን በድርጅታችን ይረዳሉ። የኮረናቫይረስ በቀላሉ የሚተላለፍ በመሆኑ በበሽታው ላለመጋለጥ በሚያድርባቸው ስጋት የተነሳ በሕሙማኑና እና በሕክምና አገልግሎት አቅራቢዎች መሃከል ሳይቀር ክፍተት ይፈጠራል።“ የብርሃን የቤት ውስጥ ህክምና አገልግሎት ድርጅት ሊቀ መንበር እና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍስሃ ወልዴ ሞላልኝ።​

በተለይ ከፍተኛ እርዳታ ለሚሹ ህሙማን በመኖሪያ ቤታቸው በመሄድ የሚሰጡ ልዩ ልዩ የህክምና እገዛዎችን ያቀፈው አገልግሎት ዛሬ ዛሬ በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው በሚተላለፈው የCOVID 19 ህመም ሳቢያ ፈተና ላይ የወደቀ ይመስላል። ​

ከአምስት መቶ በላይ የተለያዩ ህክምና አገልግሎት ዘርፍ ባለሞያዎች ያሉት "ብርሃን የቤት ውስጥ ህክምና አገልግሎት ድርጅት" በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የቤት ውስጥ ህክምና አገልግሎት ከሚያቀርቡ ድርጅቶች አንዱ ነው። ​

የብርሃን ሊቀ መንበር እና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍስሃ ወልዴ ሞላልኝ​

ድርጅታቸው የሚያቀርባቸውን ልዩ ልዩ የቤት ውስጥ ህክምና አገልግሎቶችና የኮረናቫይረስ ወረርሽኝ በተለይ በአገልግሎት ዘርፉ ላይ ያሳደረውን ጫና እና የደቀነውን ልዩ ፈተና ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ያወያዩናል።​

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የቤት ውስጥ ሕክምና አገልግሎት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዘመን - ክፍል አንድ​
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:49 0:00
የቤት ውስጥ ሕክምና አገልግሎት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዘመን - ክፍል ሁለት
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:00 0:00

XS
SM
MD
LG