በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቅዱስ ሲኖዶስ “ህገወጥ” ያላቸውን ጵጵስና አነሳ


 ቅዱስ ሲኖዶስ “ህገወጥ” ያላቸውን ጵጵስና አነሳ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:50 0:00

ቅዱስ ሲኖዶስ “ህገወጥ” ያላቸውን ጵጵስና አነሳ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ “በሕገወጥ መንገድ የጵጵስና ሹመት የሰጡና የተቀበሉ” ያላቸውን ከቤተክርስትያኒቱ መለየቱን አስታውቋል።

አባ ሳዊሮስ፣ አባ ኤዎስጣቴዎስና አባ ዜና ማርቆስ “ሥልጣነ ክህነታቸውና የማዕረግ ስማቸው በምልዐተ ጉባኤው ውሳኔ የተነሣ መሆኑ ተገልፆ ከዛሬ ጥር 18/2015 ዓ.ም ጀምሮ በቀድሞ ዓለማዊ ስማቸው እንዲጠሩ” መወሰኑን ቅዱስ ሲኖዶሱ ገልጿል።

ውሣኔውን ያነበቡት የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የኒው ዮርክ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በሕገ ቤተክርስትያን አንቀጽ 18 ንዑስ ቁጥር 5 የቤተ ክርስቲያንን ሃይማኖታዊ ሕግጋትና ቀኖና የሚያፋልስ ሊቀ ጳጳስ /ኤጲስ ቆጶስ/ ከአባልነት እንደሚሠረዝ መደንገጉን አመልክተዋል።

ውሳኔው በፍትኅ መንፈሣዊ አንቀጽ 5 ንዑስ አንቀፅ 138 መሠረት የተላለፈ መሆኑን ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG