ከናዚ ጀርመን ማጎሪያ ካምፖች አንዱና ትልቁ የሆነው “ኦሽዊትዝ” ነጻ በወጣበት በዛሬው ቀን ታስቦ የሚውለው ዓለም አቀፉ የሆሎካስት መታሰቢያ ሥነ-ስርዐት ዛሬ በአዲስ አበባ ተከናውኗል
በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ዶ/ር አብርሃም ንጉሴ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት፣ የሆሎካስት ሰለባዎች መታሰቢያ ሥነ ስርዐት “የዘር ጥላቻን የተመለከተ እንቅስቃሴ ጊዜ ሊሰጠው እንደማይገባ ዓለምን የሚያስተምር ነው” ብለዋል፡፡
ምክትል አምባሳደሩ ቶመር ባር-ላቪ ደግሞ፣ የብዙ አይሁዶችን ቤት ያንኳኳው የሆሎኮስት ግፍ ከእርሳቸው ጋራ ያገናኘዋል ያሉትን ታሪክ አስረድተዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም