በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤችአይቪ ሥርጭት ቀነሰ፤ አዲስ መከላከያ ሙከራ ላይ ነው


ሰሞኑን የወጡ ሁለት ጥናቶች በኤችአይቪ/ኤድስ መዛመት ላይ እየተመዘገበ ያለውን አዎንታዊ ስኬት የሚያሣዩ ናቸው፡፡

ከዓለም የኤችአይቪ ሥርጭት ሁለት ሦስተኛውን ድርሻ የያዙትን ከሰሃራ በስተደቡብ የሚገኙ የአፍሪካ ሃገሮችን ጨምሮ በቫይረሱ ሥርጭት ላይ በመላው ዓለም መሻሻል መመዝገቡን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል፡፡

በኤችአይቪ አዲስ የሚያገኘውና በኤድስ ምክንያትም የሚሞተው ሰው ቁጥር በእጅጉ የቀነሰ ቢሆንም ይበልጥ ትግል እንደሚያስፈልግ ግን አሳስቧል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በየዕለቱ የሚወሰደው ፀረ-ኤድስ መድኃኒት የኤችአይቪን መተላለፍ መቀነስ ማስቻሉን አንድ ጥናት አሣይቷል፡፡ ኤችአይቪ በሌላቸው ወንድ የተመሣሣይ ፆታ ወሲብ ፈፃሚዎች ላይ በመላው ዓለም በተካሄደ ጥናት ፀረ-ኤድስ መድኃኒቱ እስከ 44 ከመቶ ቫይረሱን መተላለፍ መከላከል መቻሉን ተመራማሪዎቹ ገልፀዋል፡፡

ምንም እንኳ ውጤቱ አበረታች ቢሆንም ይበልጥ ተጋላጭ በሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ የሚታየውን ለውጥ ፈትሾ ተአማኒነቱን ለማረጋገጥ አሁንም ስፋት ያላቸው ጥናቶች መካሄድ እንደሚገባቸው ሣይንቲስቶቹ ጠቁመዋል፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ሪፖርተሮች ስካት ባብ ከጆሃንስበርግ-ደቡብ አፍሪካ፤ ጄሲካ በርማን ደግሞ ከዋሽንግተን ዲሲ ያጠናቀሩት ዘገባ አለ፡፡

ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG