በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሂስፓኒክ አሜሪካውያን በምርጫው ትልቅ ድርሻ ይኖራቸዋል


በኒው ዮርክ በ2020 ምርጫ አስቀድመው ድምጽ የሰጡ የሂስፓኒክ ማህበረሰብ አባላት
በኒው ዮርክ በ2020 ምርጫ አስቀድመው ድምጽ የሰጡ የሂስፓኒክ ማህበረሰብ አባላት

በ2020 ምርጫ፣ የሂስፓኒክ ማህበረሰብ አባላት፣ አብዛኛውን ቁጥር ካላቸው ነጭ አሜሪካውያን ቀጥለው ትልቁን የመራጮች ማህበረሰብ ቁጥር እንደሚይዙ ፒው የተባለው የምርምር ማዕክል አስታውቋል፡፡ የመጨረሻው ድምጽ ሊሰጥ ጥቂት ቀናት ሲቀሩት በተሰበሰበው የኤን ቢሲ እና ዎል ስትሪት ጆርናል የህዝብ አስተያየት ድምጽ፣ በሂስፓኒክ መራጮች ዘንድ፣ የቀድሞ ምክትል ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ሁለት ለ አንድ በሆነ እጅ እንደሚበልጧቸው ተመልክቷል፡፡ የቪኦኤ ዘጋቢ ካሮላይን ፐረሱቲ ለመራጮቹ ሂስፓንኮች አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ምን እንደሆኑ በመጠየቅ የሚከተለውን አጠናቅራለች፡፡

ኩባውያን በበፍሎሪዳ ትልቁ የሂስፓኒክ ማህበረሰብ አባላት ናቸው፡፡ ብዙ ጊዜ ለሪፕብሊካን ፓርቲ እጩዎች ድምጽ በመስጠት ይታወቃሉ፡፡ ጆርጅ ሮድሪጎዝ ከነሱ መካከል አንዱ ናቸው፡፡ ስለ ነገው ምርጫ እንዲህ ይላሉ፡፡

“እኔ ለትራምፕ ነው ድምጼን የምሰጠው፡፡ ም ክን ያቱም ሶሽሊስቶች ወደ አገሬ ሲገቡ ብዙ ተስፋዎችን ቃል ገብተው ነበር፡፡ልክ ምን እንደተፈጸመ ስንገዘነዝብ ግ ን ጭምብሉን የገፈፍን ቀን በጣም ረፍዶ ነበር፡፡ ምክ ን ያቱም ሥልጣኑን በሙሉ ተቆጣጥረውታል፡፡ እዚህም አገር የማየው ተመሳሳይ ነገር ነው፡፡”

በእድሜ የገፉት የኩባ ተወላጆች፣ በተለይ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በዴሞክራቲክ ተቀናቃኛቸው ጆ ባይደን ላይ የለጠፉትን “ሶሻሊስት” የሚል ስም ያስታውሱታል፡፡ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በኩባውያን ላይ ያሳደሩትን ተጽእኖ ለመከላከል ለጆ ባይደን የምርጫ ዘመቻ ትልቅ ሥራ ሆኗል፡፡ በዚህ የተቆጡ የፍሎሪዳ የሂስፓኒክ አባላትም ዶናልድ ትረምፕን በመቃወም ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው፡፡ ሳራ ካድርድንያስ ከነዚህ መካከል አንዷ ናቸው፡፡

“ትራምፕ ወደ ሥልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ እንዲወገዱ ስጠባበቅ ነበር፡፡” ብለዋል፡፡

ከስፔይን የመጣውና ለምርጫው ሲል፣ የአሜሪካ ዜግነት ጥያቄውን አስቀድሞ በማመልከት ያገኘው አልቤርቶ ካይሮም በዚህ ምርጫ፣ ድምጽ እንደሚስጥ ተናግሯል፡፡ ማንን እንደሚመርጥም ጭምር፡

“አሁን በሥልጣን ላይ ያሉትን ፕሬዚዳንት ማባረር የሚያስፈልገን ሆኖ ይሰማኝ ነበር፡፡ ያንን በግልጽ እናገራለሁ፡፡” ብሏል፡፡

የፔንትኮስታል ቤተክርስቲያን በሆነው ቴነሲ አባል የሆኑት አንኪ ሳንዶቫል ዘወትር ማክሰኞ ወደ ዚህች ቤተከርስቲያን በመምጣት ለፕሬዚዳንቱ እንደሚጸልዩ ይናገራሉ፡፡

“እኛ እግዚአብሄር በትራምፕ በኩል ምን እያደረገ እንደሆነ አምነናል፡፡ አንድ አገር እንዲመራ መሪ የሚሰጥም ሆነ የሚነሳ እግዚአብሄርነው፡፡” ብለዋል፡፡

በ2020 ምርጫ የሂስፓንክ ማሀረሰብ አባላት፣ ከነጭ አሜሪካውያን ቀጥለው፣ ትልቁ መራጭ ማህበረሰብ በመሆናቸው፣ አሻሚና ብርቱ ፉክክር በሚጠበቅባቸው ክፍለ ግዛቶች፣ ትልቅ አስተዋጽ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ተገምቷል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ሂስፓኒክ አሜሪካውያን በምርጫው ትልቅ ድርሻ ይኖራቸዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:30 0:00


XS
SM
MD
LG